ናሽናል አቪየሽን ኮሌጅ በተለያየ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 276 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ኮሌጁ ለዘጠነኛ ዙር ተማሪዎች በአቪዬሽን፣ በቱሪዝም፣ በሎጀስቲኬስና ቢዝነሰ በሁለተኛና በመጀመሪያ ዲግሪ እን…

ናሽናል አቪየሽን ኮሌጅ በተለያየ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 276 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ኮሌጁ ለዘጠነኛ ዙር ተማሪዎች በአቪዬሽን፣ በቱሪዝም፣ በሎጀስቲኬስና ቢዝነሰ በሁለተኛና በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በሰርተፍኬት በቀንና በማታው መርኃ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬዉ እለት አስመርቋል፡፡

የናሽናል አየር መንገድ እህት ኩባንያ የሆነው ናሽናል አቪየሽን ኮሌጅ፣ ካናዳ ከሚገኘው አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር እና እንግሊዝ አገር ከሚገኘው ኢንስቲትዩት ኦፍ ኮሜርሽያል ማኔጅመንት ባገኘው እውቅና መሰረት በአቪዬሽን፣ ቱሪዝምና ሆቴል ሙያ ጋር በተገናኘ ደረጃውን ያሟላ ዓለም አቀፍ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የናሽናል አየር መንገድ ኩባንያ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኸኝ ብሩ ኩባንያዉ በኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከሚንቀሳቀሱ የግል አየር መንገዶች መካከል ግንባር ቀደም መሆኑን ጠቅሰዉ እህት ኩባንያዉ ናሽናል አቪየሽን ኮሌጅም በተለያዩ የሙያ መስኮች ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን በማሰልጠን እያስመረቀ ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህም ሃገሪቱ የተማረ የሰዉ ሃይል ለማፍራት የምታደርገዉን ጥረት በእጅጉ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
ለዚህም አየር መንገዱ በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የአቪዬሽንና የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ቀጣይነት ለማረጋገጥና ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግ ቁልፍ የሆነውን የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅን በማቋቋም ሰፊ ስራን እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከ14 ዓመታት በፊት በካፒቴን አበራ ለሚ የተጀመረው የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ አሁን ላይ ናሽናል አቪየሽን ኮሌጅን ጨምሮ በስሩ 9 ትላልቅ ድርጅቶች እንዳሉት በምርቃት በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 03 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply