You are currently viewing ናትናኤል የዓለም ዘውድ በዋስ እንዲፈታ ፍ/ቤት ቢያዝም ፖሊስ በይግባኝ እንዳይፈታ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ ከትላንት…

ናትናኤል የዓለም ዘውድ በዋስ እንዲፈታ ፍ/ቤት ቢያዝም ፖሊስ በይግባኝ እንዳይፈታ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከትላንት…

ናትናኤል የዓለም ዘውድ በዋስ እንዲፈታ ፍ/ቤት ቢያዝም ፖሊስ በይግባኝ እንዳይፈታ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከትላንት በስቲያ ማለዳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው የባልደራሱ ናትናኤል፣ ዛሬ ጠዋት ጠበቃው ባለበት ፍ/ቤት ቀርቧል። መርማሪ ፖሊስ ለፍ/ቤት ባቀረበው ክስ፣ “ናትናኤል በአድዋ ክብረ-በዓል ግዜ ህገ ወጡን ኮከብ የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ይዞ ነበር፣ እስክንድር ነጋን ተሸክሞ “ከንቲባዬ” ሲል ነበርና ሁከት ለመፍጠር ዋና ተዋናይ ሆኖ ተንቃሳቅሷልና፣ የምርመራ ሥራ እንድሰራ የ14 ቀን ቀጠሮ ይሰጠኝ” ሲል አመልክቷል። የናትናኤል ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ በበኩሉ፣ “የሰንደቅ ዓላማው ህግ እስከ አንድ ዓመት እስር ወይም ደግሞ ቀላል የገንዘብ ቅጣት የደነገገ በመሆኑ፣ ስለእስክንድር ነጋ የተባለውም የወንጀል ይዘት የሌለው በመሆኑ፣ ናትናኤል በነፃ ወይም በዋስ ሊለቀቅ ይገባል” ብሏል። ፍ/ቤቱም የሄኖክን መከራከሪያ ተቀብሎ ለናትናኤል የ5000 ሺህ ብር ዋስ ፈቅዶለት፣ ገንዘቡ ወዲያው ገቢ ተደርጓል። ሆኖም፣ ፖሊስ በውሳኔው ላይ “ይግባኝ ብያለሁ” በማለት ናትናኤል ሳይፈታ ቀርቷል። ለሰኞም ተቀጥሯል ያለው የባልደራስ ሚዲያ ክፍል ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply