ናይጀሪያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ክትባትን በጥር ወር አጋማሽ እንደምታገኝ ተገለፀ፡፡

ናይጀሪያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን በጥር ወር አጋማሽ እንደምታገኝ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡ናይጀሪያ በዚህ አመት 40 በመቶ ዜጎቿን ለመከተብ አቅዳ እየተዘጋጀች ሲሆን፤ 30 በመቶ የሚሆኑትን ደግሞ በሚቀጥለው አመት እንደምትከትብ የጤና ሚኒስትሩ ፋይስል ሲሀብ መግለጻቸው ተነግሯል፡፡

እንደ ፋይሰል ሲሃብ ገለጻ ናይጀሪያ የአጠቃላይ ህዝቧን አንድ አምስተኛ ለመከተብ ያቀደች ሲሆን የሚያስፈልጓትን 42 ሚሊዮን ክትባቶችን እንደምታገኝም ተስፋ ማድረጓ ተገልጿል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ክትባት የተገኘው ከአለም አቀፍ የክትባት መጋራት ጥምረት ኮቫክስ በኩል ሲሆን፤ ጥምረቱም የፋይዘር ባዮቲክ 100ሺህ ክትባቶችን ወደ ናይጀሪያ እንደሚልክም ቢቢሲ ዘገቧል፡፡

************************************************************************

ቀን 30/04/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply