ናይጄሪያውያን ውዝግብ ላስነሳው የምርጫ ውጤት በትዕግስት እንዲጠብቁ የዩስ አምባሳደር ተማጸኑ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-1825-08db1e3f56a3_w800_h450.jpg

ምርጫውን ተከትሎ በርካታ በውጤቱ  የተቆጡም ደስታውቸውንም እየገለጡ ያሉ ዜጎች እንዳሉ  የተናገሩት በናይጄሪያ  የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ውዝግቡ ሙግቶች በህጋዊ ሂደት ውሳኔ እስኪያገኝ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ሜሪ ቤት ሌነርድ “የምርጫ ሂደት ፍርድ ቤት ደረጃ ሲደርስ ላያመረቃ ይችላል፡፡ ነገር ግን በህግ የበላይነት በሚመራ ህገ መንግሥታዊ ዲሞክራሲ ትክክለኛው አሰራር እርሱ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ነጻው የናይጄሪያ የምርጫ ኮሚሽን በፕሬዚደንታዊ ምርጫው ቦላ አህመድ ቲኑቡ ማሸነፋቸውን አውጇል፡፡

“ምርጫው ተጨበርብሯል” ያሉት ተቃዋሚ መሪዎች በበኩላቸው በፍርድ ቤት እንሟገታለን ብለዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply