ናይጄሪያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያዋስኗትን ድንበር ዳግም ከፍታለች

ናይጄሪያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያዋስኗትን ድንበር ዳግም ከፍታለች

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ናይጄሪያ ከቤኒን እና ከኒጀር ጋር የሚያዋስኗትን የድንበር ማቋረጫዎች እንደገና ከፍታለች።

አሁን ላይ የተከፈቱት አራት የድንብር መቋረጫዎች ሲሆኑ በህገ-ወጥ መንገድ ይደረግ የነበረውን የግብርና ምርቶች እና የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለማስቆም በሚል የተዘጋ ነበር፡፡

ሌሎች የድንበር አካባቢዎች በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ እንደገና ይከፈታሉ ነው የተባለው፡፡

ናይጄሪያ ከተወሰነ ጊዜ እምቢተኝነት በኋላ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና አባልነቷን አጽድቃለች ፡፡

ነፃ የንግድ ቀጠና በጥር ወር በይፋ ሥራውን ከጀመረ በዓለም ላይ ሁለተኛው ትልቁ ነፃ የንግድ ቀጠና ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ይህም በአፍሪካ ውስጥ ያለውን የንግድ ልውውጥ እሴት በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመላክቷል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ናይጄሪያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያዋስኗትን ድንበር ዳግም ከፍታለች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply