ኔቶ ከሩስያ ድንበር 60 ኪሎ ሜትሮችን በሚርቀው የኢስቶኒያ ግዛት ውስጥ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል:: ጉዳዩን በተመለከተ ከሩስያ ጋር የሚያያዝ አይደለም ብሏል ኔቶ:: ኢስቶኒያ የምታስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Jq1Oa4wMygiL8jkgRC2VlKvyGiz1o9CNs5YQSeCq3xyuF35YpsBzicfA1767NvD8fDFBcoa5GUC4Nd7VDfZhBq8RfodENDosbyiv23Iog5xR8cokzm5o_ueyOSonvv3JNdrIyGra08JxixcsA4jmEq3qC43lsqxSr7fd7tPGyZqWA8YRD5vClPNIWanv77kTQmC1B15Q8AP0JG6PfH0gtQoTIIEl-Lc6ngIJrxINgwx0Yv-UimhFdcdt1Yvk0iK31uVcHUmzTN09rknFUCLPALW783MK8NFz66kHfVd1T9LYD9UmDxcI1KQBBcxdbErUnSZWiOJ6hvxnV3-DgOu9Eg.jpg

ኔቶ ከሩስያ ድንበር 60 ኪሎ ሜትሮችን በሚርቀው የኢስቶኒያ ግዛት ውስጥ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል::

ጉዳዩን በተመለከተ ከሩስያ ጋር የሚያያዝ አይደለም ብሏል ኔቶ::

ኢስቶኒያ የምታስተናግደው ይህ ወታደራዊ ልምምድ በምድር የባህር ፣ አየር እና የሳይበር ተከላካይ ወታደሮችን ጭምር ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ልምምዱ ከ15ሺህ በላይ ወታደሮችን ከ 14 በላይ የኔቶ እና ከኔቶ ውጭ የሆኑ ሃገራትን ፊንላንድን እና ስዊድንን ጭምር ያቀፈ ነው፡፡

ይህኛው ልምምድ ሩስያ በዩክሬን እያካሄደች ካለችው ወታደራዊ ዘመቻ ጋር የሚያያይዘው ነገር እንደሌለም እወቁልኝ ብሏል ኔቶ፡፡

ከ20 በላይ ሃገራት እና ከ30 ሺህ በላይ ወታደሮች የተሳተፉበት ኔቶ ያሰናዳው ስልጠና ከዚህ ቀደም መካሄዱን ቢቢሲ በዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply