ኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ የማስተር ክላስ ስልጠናውን በይፋ ጀመረ

ከተከፈተ 17ኛ ዓመቱን ያስቆጠረውና እስካሁን ከ3ሺ800 በላይ የፋሽን ዲዛይነሮችን አሰልጥኖ ያስመረቀው ኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ ፤ አዲሱን የማስተር ክላስ ሥልጠናውን ቅዳሜ ምሽት ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ቦሌ ዩጎ ሰርች አጠገብ በሚገኘው ሪያሊቲ ፕላዛ ህንጻ ላይ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

የፋሽን ማስተር ክላስ ከሚሰጣቸው ሥልጠናዎች መካከል፡- ስፔሻል ፓተርን ዲዛይን፣ አርት ድሮዊንግ፣ ፋብሪክ ፔይንቲንግ፣ ፋሽን ስታይሊንግ፣ 3ዲ ዲዛይን፣ ፋሽን ማኔጅመንትና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ መሥራችና ባለቤት ወ/ሮ ሣራ መሃመድ በምሽቱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “ማስተሪንግ ክላስ ሰዎች እንደ መክሊታቸው (ተሰጥኦዋቸው) ሥልጠና የሚያገኙበት ፕሮግራም ነው” ብለዋል፡፡

በምሽቱ በኔክስት ፋሽን ዲዛይን ኮሌጅ ተመራቂዎች የተዘጋጀ ለየት ያለ የፋሽን ትርኢት ለታዳሚዎች ቀርቧል፡፡

ኮሌጁ ከዓለማቀፍ ተመሳሳይ የማሰልጠኛ ተቋማት ጋር በፈጠረው መልካም የሥራ ግንኙነት 42 ዲዛይነሮች በህንድ አገር ሙሉ የነጻ ትምህርት እንዲያገኙ በማድረግ ሥልጠናቸውን ተከታትለው በመመለስ ለኢንዱስትሪውና ለአገራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ኮሌጁ ባለፉት ዓመታት  ከሥልጠናው ጎን ለጎን የተለያዩ የፋሽን ትርኢቶችን ከአገር ውስጥ ባሻገር በኒውዮርክ፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኡጋንዳና ሌሎች አገራትም ማቅረቡ ታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply