ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው መመርያ ምክንያት ኢንዱስትሪዎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ተባለ፡፡

ሚኒስቴሩ የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው፣ ለአገር ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ታቅዶ ከነበረው 157,500 ኩንታል ጨው ውስጥ 99,800 ኩንታል የቀረበ ሲሆን ይህም የዕቅዱን 63.4 በመቶ ነው፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው ‹‹የጨው ግብዓት መመርያ›› ከአፋር ክልል ውጪ ያሉትን የጨው አቀነባባሪዎች ያገለለ መሆኑ በችግርነት ተጠቅሶ፣ ከዚህ በፊት በሁሉም ክልሎች ከሚገኙ አቀነባባሪዎች የታጠበ ጨው ሲወስዱ የነበሩ የኬሚካል፣ የጨርቃ ጨርቅና የመጠጥ ኢንዱስትሪዎች ለችግር ተጋላጭ እንዲሆኑ ማድረጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል መናገራቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም ከዚህ በፊት በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅራቢ ልማት ድርጅት ይቀርብ የነበረው ጨው፣ የአፋር ክልል አዲስ ባደራጃቸው መሥሪያ ቤቶች እንዲቀርብ የሚል ውሳኔ በክልሉ በመወሰኑ፣ ድርጀቶች ምንም ዓይነት ጨው እያቀረቡ አለመሆኑ፣ በዚህም ሳቢያ የጨው አቅርቦት 63 በመቶ ዝቅ እንዲል በማድረግ የግብዓት አቅርቦት ችግር መፈጠሩን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply