ንግድ ሚንስቴር በነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ ላይ ከነገ ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 30 የሚቆይ የዋጋ ክለሳ ማድረጉን አስታውቋል። በክለሳው መሠረት፣ ቤንዚን በሊትር 34 ብር ከ71 ሳንቲም፣ ነጭ ና…

https://cdn4.telesco.pe/file/D4m6JTghDHh7RMgq_I9SL2KpRct4gbpnAxWKVv0KXTR5tFQA-3kGmDQ9-J9Qwu6V7ISKWlYC4m4tytIENq7kYF22zal1gOlM-X1I65blJ_YVJhCCLsdgZmC5iO9MT2o03OyRU7wQszJWpfkm4SRitIyuMYZyNrGki9N4XJ4qdS2CEKcF84A1TdZCD3YcMjfGGmZWqB0LZCyftfXfsDexHURmXZg3eV8EkLSXaWtu4qEmW_AhkkooOWutfTS1ss-xsd_0fTWeb4iUu-xBZb0byKtJ2fmaev8d6leHEcdS4P9AWdJisE0fXJlDASg0iLUF5SQqoeU88y_ZR7LKVnLUCg.jpg

ንግድ ሚንስቴር በነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ ዋጋ ላይ ከነገ ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 30 የሚቆይ የዋጋ ክለሳ ማድረጉን አስታውቋል።

በክለሳው መሠረት፣ ቤንዚን በሊትር 34 ብር ከ71 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ እና ኪሮዚን 28 ብር ከ84 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ73 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ29 ሳንቲም እና የአውሮፕላን ነዳጅ 58 ብር ከ77 ሳንቲም እንደሚሸጡ ተገልጧል።

የዋጋ ክለሳ የተደረገው፣ ዓለማቀፍ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ መጨመር በሀገሪቱ የነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ ኪሳራ በማስከተሉ፣ የሀገር ውስጡ የችርቻሮ ዋጋ ከጉረቤት ሀገራት ዋጋ እስከ 100 ፐርሰንት ድረስ የሚያንስ እና ምርቱ ለኮንትሮባንድ ንግድ የተጋለጠ በመሆኑ እና የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ሚንስቴሩ አብራርቷል፡፡

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply