ኖህ ሪል ስቴት ግንባታቸው የተጠናቀቁ 754 አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶችን አስረክቧል፡፡
ባለፉት 10 ዓመታት ከ8 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ጥራት የተገነቡ ቤቶችን በሰዓቱ ማስረከቡን የገለጸው የሪል ስቴት ድርጅቱ፣ይህም በሃገሪቱ የቤት ልማት ዘርፍ ላይ ቁልፍ ተዋናይ ሆኜ እንድቀጥል አስችሎኛል ብሏል፡፡
የኖህ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍጹም አውግቻው፣ ኩባንያው በኖህ ግሪን ፓርክ ሳይት አዲስ የተገነባውን የመኖሪያ መንደር በይፋ ሲያስመርቅ፣ ባለፉት 10 ዓመታት ለተሰሩ ስራዎችና ለነበረውን የስኬት ጉዞ የምናከብርበት እንዲሁም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ለራሳችን ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት ነው ብለዋል፡፡
ኩባንያው በ2020 ዓ.ም 30 ሺህ ቤቶችን ገንብቶ ለማስረከብ ትልቅ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ እንደሚገኝም ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
በሚቀጥሉት 4 ዓመታት ለማልማት ከታቀደው 3 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ የሚሆነው ለመኖሪያ ቤት መገንቢያ ሲሆን፣ አንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ያህል ደግሞ የንግድ ማዕከላትን ለመገንባት ይውላል ተብሏል፡፡
31 ፕሮጀክቶችን በጥራትና በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ማጠናቀቅ መቻሉ የኩባንያውን ስኬታማ ጉዞ ማሳያ ነው ያሉት ዋና ስራ አስጻሚው፣በአሁኑ ወቅትም በጉርድ ሾላ፣በሰሚት፣በቦሌ፣በፍላሚንጎ፣በቀበና እና በእንቁላል ፋብሪካ ግንባታዎችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video