“አሁንም በጽናት ወደፊት እስከ ትግላችን መዳረሻ ፍትህ ነጻነትና እኩልነት ድረስ እንጓዛለን።” ራያ ጢነኛ_የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…     ጥር 9 ቀን…

“አሁንም በጽናት ወደፊት እስከ ትግላችን መዳረሻ ፍትህ ነጻነትና እኩልነት ድረስ እንጓዛለን።” ራያ ጢነኛ_የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 9 ቀን…

“አሁንም በጽናት ወደፊት እስከ ትግላችን መዳረሻ ፍትህ ነጻነትና እኩልነት ድረስ እንጓዛለን።” ራያ ጢነኛ_የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጥር 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ራያ ጢነኛ_የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ ከእውቅና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ያቀረበው ቅሬታ:_ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሃይል ሚሊሻና ፋኖ እንዲሁም የአፋር ልዩ ሃይል በወሰዱት ህግ የማስከበር እርምጃ ላይ ከሰራዊቱ ጎን ለጎን የህዝቡ ሚና ከፍተኛ ነበር። በዚህ ህግ የማስከበር እርምጃ ላይ በራያ ግንባር በኩል የራያ ህዝብ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በዚህ ሂደትም የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን የራያ ጢነኛ(የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ) ለሰራዊቱ ድጋፍ ከማሰባሰብ ጀምሮ ከተለያዩ አካባቢ ድጋፍ ይዘው የሚመጡ አቻ ወጣት ማህበሮችንና ሌሎች እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ ከፍተኛ ሚና ተወጥቷል። ይሁንና ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብና ተጽእኖ ያልወጡትና መውጣት የማይፈልጉት አብዘሃኛዎቹ የቆቦ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ለዚህ በጎ ተግባር እውቅና በሰጡበት ፕሮግራም የራያ ጢነኛ(የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ) የሰራዉን መልካም ተግባር ወደ ጎን በመተው ለቆቦ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የእውቅና ሽልማቱን በመስጠት አለመለወጣቸዉን በተግባር አሳይተዋል። የራያ ጢነኛ( የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ) ያልተለወጡ የቆቦ ከተማ አስተዳደር አመራሮችን እውቅና ተማምኖ ትግል አልጀመረም። በጣም ብዙ ግፍ እየሰሩብን ተቋዉመን ከዛሬ እንደደረስን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። አሁንም በጽናት ወደፊት እስከ ትግላችን መዳረሻ ፍትህ ነጻነትና እኩልነት ድረስ እንጓዛለን። በኛ (በራያ ጢነኛ) እምነት ግን አስተሳሰባችንና አሰራራችን ሰፊና ሁሉን አቃፊ ፓርቲን ሳይሆን ህዝብን መሰረት ያደረግን ስለሆነ ማንኛዉም የራያ ቆቦ ወጣት ስኬቱ ስኬታችን ዉድቀቱ ዉድቀታችን እንደሆነ ስለምናምን እውቅናዉን ያገኙትን ወጣቶች በርቱ ለማለት እንወዳለን። በመጨረሻም/መውጫ ባለፉት 30 አመታት በቅርቡ የተደመሰሰው ትህነግ/ህወሃት አማራ ተግባብቶ እንዳይሰራ እንዳይናበብ በህግም ይሁን ከህግ ዉጭ ሰፊ ስራ እንደሰራ ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ነው፡፡ ዛሬ ግን ሌላ ቀን ሌላ ጊዜ ነው። ሁሉም ነገር መስተካከል እንዳለበት እናምናለን። አማራ በአራቱም አቅጣጫ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመበት ባለበት በዚህ ጊዜ ለብቻ ጉዞ የህዝባችንን የመካራ ጊዜ ይጨምረዋልና በመደራጀት በመስማማትና በመናበብ አንድ ሆነን ቆመን የተጀመረዉን ትግል ዳር ማድረስ አለብን መልእክታችን ነው፡፡ “የራያ ጢነኛ (የአማራ ወጣቶች ማህበር በራያ ቆቦ)”

Source: Link to the Post

Leave a Reply