አሁንም በ40 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድጋሚ ምርጫ ማድረግ አልተቻለም፡፡

የድጋሚ ምርጫ ይካሄድባቸዋል ከተባሉ የምርጫ ጣበያዎች ውስጥ በ40ዎቹ አሁንም ምርጫው አለመደረጉን ነው የተገለጸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ባሳለፍነው ቅዳሜ በሰጡት መግለጫ ላይ፤ የፀጥታ ችግሮች ባለመስተካከላቸው አሁንም ምርጫ የማይደረግባቸው አካባቢዎች መኖራቸውም ተነስቷል።

አስቻይ ሁኔታዎች ሲኖሩ የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተቀሩ ቦታዎች ምርጫ ለማካሔድ ቦርዱ ይሰራል ብለዋል።

አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት በተመለከተም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

የቀሪና ድጋሚ ምርጫ ሂደቱ በአራቱ ክልሎች በ29 የምርጫ ክልሎች እና በ1 ሺህ 218 የምርጫ ጣቢያዎች መካሄዱን ገልፀዋል።

የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በትናንትናወረ ዕለት ተካሂዷል።

ምርጫ ሂደቱ በአራቱም ክልሎች በ29 የምርጫ ክልሎችና በ1 ሺህ 218 የምርጫ ጣቢያዎች መካሄዱን ነው የተናገሩት፡፡

ሔኖክ ወ/ገበርኤል

ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply