አሁንም ዲያስፖራ ልብ ግዛ ! ====== ሸንቁጥ አየለ ========= ሸዋ ዉስጥ ለተፈጠረዉ የፋኖዎች አለመግባባት ቁልፍ መነሻዉ ዲያስፖራዉ ነዉ::… ዲያስፖራዉ በቡድን እየተቧደነ አንዳ…

አሁንም ዲያስፖራ ልብ ግዛ ! ====== ሸንቁጥ አየለ ========= ሸዋ ዉስጥ ለተፈጠረዉ የፋኖዎች አለመግባባት ቁልፍ መነሻዉ ዲያስፖራዉ ነዉ::… ዲያስፖራዉ በቡድን እየተቧደነ አንዳንዴም በዝንጀሮ ፍቅር አብሮ እየከነፈ አንዱን አንጋሽ አንዱን አኮሳሽ እየሆነ ብዙ ስህተት ፈጥሯል::ይሄ ለብዙ ወራት የቆዬ የተሳሳተ አካሂያድ እንጂ በቅርብ የተከሰተ አይደለም:: ==== እነ እከሌ በእነ እከሌ ስር ካልገቡ መመታት አለባቸዉ የሚለዉን መርዛማ ሀሳብ ቀምረዉ ወደ ፋኖዉ ይዘዉ የወረዱት እና ያሰራጩት ዲያስፖራዉ ዉስጥ ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ናቸዉ:: አንዳንዶች መልካም ያደረጉና የተጠናከረ እዝ የፈጠሩ መስሏቸዉ በድንቁርና አንዳንዶችም ግለሰቦችን ከማምለክ በሽታ አንዳንዶችም የግላቸዉን ጉዳይ እያሰለሉ:: ====================== የሁሉንም ስም ዝርዝር ማቅረብ ይቻላል::ሆኖም ዲያስፖራ ያለዉ የተለያዬ ቡድን ደግሞ ከእነ ድንቁርናዉ እና ከነ ክፋቱ የፋኖን ትግል በጅጉ እያገዘ ያለ ሀይልም ነዉ::ስለዚህ ዲያስፖራዉ እንዲታረም ብቻ ነዉ የምንመክረዉ::ዲያፖራዉ ቀጫጫ ሀሳቦቹን ወደጎን ገፍቶ በሜዳ ግንፍል ግንፍል የሚለዉን ርባናቢስ ንዴቱን ከዬኪሱ አዉጥቶ በመጣል በትእግስት የድጋፍ ስራዉን ላይ ብቻ እንዲያተኩር በእግዚአብሄር ስም ይጠዬቃል:: ========= ፋኖዉን ያስነሳዉ መድሃኒዓለም ነዉና መሪዉም መድሃኒዓለም ብቻ ነዉ:: ፋኖዉን ማንም አላስነሳዉም:ማንም አላደራጀዉም ማንም ድርጅት የአኔ የግሌ ነዉ ሊለዉም አይችልም:: ============= መድሃኒዓለም ኢትዮጵያን ለማዳን እየተዘጋጀ ነዉ::ፋኖዉ ደግሞ ኢትዮጵያን ለማዳን ቁልፍ እንዲሆን መድሃኒዓለም ቀድሞ ያስነሳዉ ሃይል ነዉ::ገና ቀጣይ የነጻነት ሀይል በመላ ኢትዮጵያ ይነሳል::ኢትዮጵያ በደስታ እልል ታላለች::ጠላቶቿም ይንቀጠቀጣሉ::ጠላት ሁሉ ከሰሜንም ከደቡብም:ከመሃልም:ከምስራቅም:ከም ዕራብም ቢሆን በኢትዮጵያ ምድር መድሃኒዓለም ምን እንደሚሰራ አያስተዉልም::እዉነተኛ ኢትዮጵያ ሁሉ ግን ሀገርህ ትድንልህ ዘንድ ከእግዚአብሄር ዐላማ ጋር ተባብረህ ቁም:: ሽልፍጥ ግልፍጥ ዉልፍጥ ልምጥ ልምምጥምጥ አትበል:: ——– ኢትዮጵያም በጣም በፍጥነትት ወደ ከፋ ጦርነት እና መፈራረስ ዉስጥ በዐቢይ አህመድ እና በኦነግ/ኦህዴድ አመራር እየገባች ነዉ::ፋኖዉን ደግሞ እግዚአብሄር የጦር ልምምድ እንዲያገኝ አድርጎ እያዘጋጀዉ ነዉ:: ===== ፋኖ ልበ በል::እርስ በርስ የሚከፋፍልህን ማንንም እንዳትሰማ::አንተ ላይ እግዚአብሄር አላማ አለዉ:: ==== የዲያስፖራ ወንድሞችህ የሚያቀርቡልህን ድጋፍ ሁሉ በአክብሮት ተቀበል::የአመራር ሚስጢርህን:ድርጅታዊ ሚስጢርህን ግን ሸሽገህ ያዝ::በመላዉ አማራ ያለህ ፋኖ እርስ በርስህ ተናበብ:: በተለይም በመላዉ ሸዋ ያለህ ፋኖ ፈጥነህ ተነጋገር::ሽማግሌ እንዳትፈልግ::እከሌ በእኔ ስር ይሁን እከሌ በእከሌ ስር ይሁን የሚለዉን ሙትቻ ሀሳብ እርሳዉ:: ሂደቱ እራሱ ሁኔታዉን ያመቻቸዋል::የሚሆናችሁንም መሪ እርስ በርሳችሁ እንድትመራረጡ እግዚአብሄር ይመራችኋል::አንተ የእግዚአብሄር ህዝብ ነህ::የእግዚአብሄር ህዝብ ደግሞ መሪ አለዉ::እሱም እግዚአብሄር ነዉ:: ====== በጥቅሉ አሁንም ዲያስፖራ ልብ ግዛ :: ፋንዉን በማስታጠቅ ቁልፍ ስራ እየሰራህ ነዉና በርታ::ተንኮሏን: እርስ በርስ መጓተቷን:ሿሚና ሻሪ ልሁን የሚትለዋን የድንቁርና ስራህን ግን ተዋት::አንድ እየደመርህ እንደ ብትቀንስ የቆምክበት ነጥብ ላይ ሁሌም እንደመርገጥ ይሆንብሃል እና የምትችለዉን በቅንነት ስርተህ ዝም በል::ቀሪዉን ለእግዚአብሄር መስጠትን ተለማመድ::

Source: Link to the Post

Leave a Reply