
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ለገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ተጠያቂው ትህነግ ብቻ ሳይሆን ምሁራንም ናቸው ሲሉ ኮማንደር ሻውል ጌታቸው ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር 30/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለበርካታ ዓመታት በከፍተኛ ሀላፊነት ያገለገሉት፤ የአማራ ልዩ ሀይልን አደረጃጀት የሰሩትና የ‹‹የኢትዮጵያ አጼዎችና ሊህቃኖቿ ›› የሚል የኢትዮጵያን ፖለቲካ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መጽሀፍ የጻፉት ኮማንደር ሻውል ጌታቸው ከአሻራ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አሁን ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለገባችበት ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ዋነኛ ተጠያቂው ትህነግና ትህነጋዊያን ብቻ ሳይሆኑ ምሁራን ጭምር እጃቸው አለበት ብለዋል፡፡ በተለይም በህገ መንግስት የተደገፈ በደል በአማራው ህዝብ ላይ ሲፈጸም ምሁራን የፈጠሩት ክፍተትና የትህነግ ፖለቲካዊ ሴራ ሳይገባቸው ያደረጉት ፖለቲካዊ ተሳትፎ ሀገሪቱን ለፖለቲካዊ ኪሳራ ፤አማራውን ደግሞ ለመሞትና ለመፈናቀል ዳርጎታል ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ህገ መንግስታዊ የሆኑ ጥያቄ ተነስቶላቸው ኮማንደር ሻውል ‹‹ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ በተለይም በአማራው ህዝብ ጥያቄ ሆነው የሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች ከህገ መንግስቱ ውጭ የሆኑ እንደሆኑ ለአብነትም የአማራ ርስት የሆኑት ወልቃይት፤ጠለምት ፤ ራያ አላማጣ እና መተከል ህገ መንግስቱን መሰረት አድርገው የተወሰዱ ሳይሆኑ በጉልበት የተወሰዱ ስለመሆናቸው ገልጸው አሁን ላይ አስረኛ ክልል ተብሎ ለሲዳማ የተሰጠውም ከህገ መንግስቱ ውጭ ነው›› የሚል ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የ1960ዎቹ ፖለቲከኞች የፈጠሩት ክፍተት ለአሁኑ የአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ የህሎና አደጋ አጋልጦታል የሚሉት ኮማንደር ሻውል ወጣቱ ትውልድ አወንታዊ በሆነ የፖለቲካ እሳቤ ውስጥ ራሱን ማሳለፍ አለበት ብለዋል፡፡ ትህነግ የመጣችውና ለሰላሳ ዓመታት ሀገሪቱን የገዛች በአማራ እና በሌሎች ምሁራን ተሳትፎ እና ከፍተኛ ድጋፍ ነው የሚሉት ኮማንደር ሻውል ለትህነግ መውደቅም የምሁራን አስተዋዕጾኦ ጉልህ ድርሻ አለው ሲሉ ምሁራን በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን የቀደመ እና አሁናዊ የፖለቲካ ሚና ገልጸዋል፡፡ ትህነግ የአማራን ህዝብ ባህል፤ ወግ፤ መልካም እሴት፤አቃፊነትና ሌሎች አማራዊ የሖኑ ማንነቶችን ለመደፍጠጥ ከፍተኛ ሸፍጥ ሲሰራ እንደነበር እና በአማራው ላይ ሌሎች ህዝቦች የግድያ ፤የመዝረፍና የማፈናቀል ተግባር እንዲፈጽሙ በማድረግ አማራው እንዲነሳ እና አማራ ነኝ በሚል በአንድነት ሌሎችን ህዝቦች እንዲጨፈጭፍ ለማድረግና ባህል፤ወግ እሴቱን ለማጠልሸት ሲሆን አማራው እንደ አማራ በመደራጀት መልካም የሆኑ እሴቶችን ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን እያስቀጠለ እስካሁኗ ደቂቃ መገኘቱ አንድም የህወሃት ዓላማ መክሸፉን የሚያሳይ ሲሆን ሁለትም አማራው ማንንም ህዝብ የመግደልና የመበቀል ስሪትና ታሪክ እንደሌለው ማሳያ ሆኗል ብለዋል፡፡ የተከበራችሁ የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮቻችን ከኮማንደር ሻውል ጌታቸው ጋርያደረግነውን የሁለት ክፍል ውይይት በአሻራ ሚዲያ የዩቱዩብ ገጽ ላይ በመግባት እንድትከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ ከተወሰኑት የሚከተለውን አደረግሁ ባቸው። ግን ዪትዩቡ ሪዳይሬክት አያረግም ዘወትር አዳዲስ መረጃ እንዲደርስዎ https://t.me/asharamedia24 በመጫን ይቀላቀሉን። ዩትዩብ፥ https://bit.ly/33XmKro ላይክ እና ሰብስክራይብ ያድርጉን ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው
Source: Link to the Post