“…አሁን ላይ እየተሰራ ያለውና ሊሰራ የታሰበው እንዲሁም በስራ ቦታችን እየተሰጠን ያለውን ትዕዛዝ ስሰማ ልቤ በሀዘን ተዋጠ እና መረጃውን ለቤተክርስቲያን ታደርስልኝ ዘንድ እማፀንሀለሁ።…..

“…አሁን ላይ እየተሰራ ያለውና ሊሰራ የታሰበው እንዲሁም በስራ ቦታችን እየተሰጠን ያለውን ትዕዛዝ ስሰማ ልቤ በሀዘን ተዋጠ እና መረጃውን ለቤተክርስቲያን ታደርስልኝ ዘንድ እማፀንሀለሁ።…” ከአንድ የፌደራል ፖሊስ አባል_በውስጥ የደረሰን መልዕክት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ወንድሜ እኔ በፌደራል ፖሊስ ውስጥ ተቀጥሬ ለሀገሬ ህዝብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ጎሳ ሳለይ ለቆምሁለት የህግ ጥበቃ እየሰራሁ የምገኝ ነኝ። ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየተደረገ እና ሊደረግ ያሰበውን በቅርብ ሆኜ እየተከታተልሁ እገኛለሁ። እናም እጅግ ይዘገንናል። እኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ነኝ። እኔም ጊዜ ኖሮኝ ቆሜ ባላስቀድስም ጠዋት ለነግህ ምሽት ለሰርክ ተገኝቼ ወንጌል ባልሰብክም ባላገለግላትም እናትና አባቶቼ የአቆዩኝ አንዲት ሐይማኖት፣ አንድ ፓትሪያሪክ፣ አንድ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሆኗን ነው የማውቀው። አሁን ላይ እየተሰራ ያለውና ሊሰራ የታሰበው እንዲሁም በስራ ቦታችን እየተሰጠን ያለውን ትዕዛዝ ስሰማ ልቤ በሀዘን ተዋጠ እና መረጃውን ለቤተክርስቲያን ታደርስልኝ ዘንድ እማፀንሀለሁ። ነገሩ እንዲህ ነው በሚቀጥለው የካቲት 5 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን በሲኖዶስ ላይ የተቃጣው ጥፋት በመንግስት በኩል አፋጣኝ መልስ ካልተሰጠ በቅዱስ ጳጳሱ መሪነት አለማቀፋዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንወጣለን በተባለው መሰረት ይህን ሰልፍ ለማስቀረትና ቀጥታ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ የመጨረሻ ዝግጅቱ አልቋል። እንዲሁም በተጨማሪ ደግሞ የህገወጡ ቡድን ደጋፊ ከኦሮሚያ ክልል ህዝብ እያመጡ ስልጠና እየተሰጠ ነው። ይህም በእሁዱ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ የህገወጡን ቡድን እየደገፈ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ የሚቃወምና መብታችን ይከበር የሚል ስራ በፍጥነት እየተሰራ ነው። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ በሁሉም ክፍለ ከተማ ያሉ የአማራ ተወላጆችን ከቀን ሰራተኛ አንስቶ ደጅ ላይ ቡና የምታፈላ ሴት ሳትቀር ጥቁር አትልበሱ በሚል ሰበብ እየያዛችሁ እሰሩ ተብለናል። ምክንያቱም በእሁዱ ሰልፍ ላይ ብዙ ህዝብ መገኘት የለበትም ብለዋል። እናም አደራ ይሔን መልክት ለሚመለከተው ሁሉ አድርስልኝ ሲል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት ስም ጠይቋል። የብልፅግና ውድቀት ከቤተክርስቲያን ጋር ሲጣላ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply