አሁን ሕግ የማስከበር እርምጃው ወደ 3ተኛና ወሳኙ ምእራፍ ተሸጋግሯል ሲሉ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ…

አሁን ሕግ የማስከበር እርምጃው ወደ 3ተኛና ወሳኙ ምእራፍ ተሸጋግሯል ሲሉ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…

አሁን ሕግ የማስከበር እርምጃው ወደ 3ተኛና ወሳኙ ምእራፍ ተሸጋግሯል ሲሉ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሦስተኛው ምእራፍ በመቀሌ የሚካሄደውና የክህደት ቡድኑን ለሕግ ለማቅረብ የሚደረግ የመጨረሻው እርምጃ ነው ያሉ ሲሆን የዚያኑ ያህል ከፍተኛ ጥበብ፣ ጥንቃቄና ትእግሥት የሚፈልግ እንደሆነ ግልጽ ነው ሲሉ አክለዋል። “ህወሐት በመቀሌ ከተማ ውስጥ የሃይማኖት ተቋማትን፣ ሆቴሎችን፣ የመንግሥት ተቋማትን፣ የሕዝብ መኖሪያ መንደሮችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ቅርሳ ቅሶችንና መካነ መቃብሮችን ሳይቀር እንደ ምሽግ ተጠቅሞባቸዋል።መጥፋቱ ላይቀር ብዙዎችን ይዞ ለመጥፋት ተዘጋጅቷል።” ሲሉም ገልፀዋል። በመሆኑም፤ 1ኛ፡- የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች፥ በጀመርነው ሕግን የማስከበር እርምጃ ቁልፍ ተዋናዮች እንድትሆኑ፣ ከሠራዊታችን ጎን በመቆም ይሄንን የክህደት ቡድን አባላት ለፍርድ በማቅረብ ወሳኝ ሚናችሁን እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን። ለጥቂት ስግብግብ ጁንታዎች ሲባል አንድም ሰው መሞት፣ አንዲትም ንብረት መውደም የለበትም። ለዚህም የእናንተ ትብብር አይተኬ ሚና የሚጫወትና ብዙ ጉዳቶችን እንደሚያቀል እሙን ነው። 2ተኛ. የክህደት ቡድኑን ዓላማ በማስፈጸም ላይ ያላችሁ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አባላት፥ አሁንም ቢሆን እጃችሁን በሰላም ለመስጠት ጊዜው አልረፈደም። ሕግ የማስከበር እርምጃው የመጨረሻ ምእራፍ ላይ መሆናችንን ተረድታችሁ የማያዳግመውን ዕድል እንድትጠቀሙበት፤ ከአሁኗ ሰዓት ጀምሮ ባለው በ72 ሰዓታት ውስጥ እጃችሁን በሰላም ለመንግሥት እንድትሰጡ የመጨረሻ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን። 3ተኛ፡- የጁንታው አባላት፥ የጥፋት ጉዟችሁ ጀንበሯ እየጠለቀች መሆኑን አምናችሁ፣ ከማትወጡበት ቅርቃር ውስጥ መግባታችሁን ተገንዝባችሁ በቀጣይ 72 ሰዓታት ውስጥ እጃችሁን በሰላም እንድትሰጡ እንጠይቃችኋለን። የመጨረሻዋን ዕድል ተጠቀሙበት። ተጨማሪ የሕዝብ እልቂት ከመፍጠርና ከተማ ከማውደም ተቆጥባችሁ ከታሪክ ውግዘት እንድትድኑ ሲሉ ነው ጠ/ሚኒስትሩ ጥሪ ያቀረቡት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply