#አሁን የደረሰን መረጃ በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ በዛሬው ዕለት ጥቅም 30 / 2013 ዓም በወረዳው አመራሮች አስተባባነት ሊፈጸም የነበረ ጥቃት ከሸፈ።…

#አሁን የደረሰን መረጃ በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ በዛሬው ዕለት ጥቅም 30 / 2013 ዓም በወረዳው አመራሮች አስተባባነት ሊፈጸም የነበረ ጥቃት ከሸፈ።…

#አሁን የደረሰን መረጃ በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ በዛሬው ዕለት ጥቅም 30 / 2013 ዓም በወረዳው አመራሮች አስተባባነት ሊፈጸም የነበረ ጥቃት ከሸፈ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 30 2013 ዓም ባህር ዳር በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ በዛሬው ዕለት ጥቅም 30 / 2013 ዓም በወረዳው አመራሮች አስተባባነት ሊፈጸም የነበረ ጥቃት በህብረተሰቡ ንቃት መክሸፉን አይን እማኞች ለአሻራ ሚዲያ ገለጹ ። በጉራ ፋርዳ ከአሁን በፊት ማንነታቸው ብቻ ተለይቶ የተገደሉት አማራ ዎች ጉዳይ እልባት ሳያገኝ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 30 /2013 ዓም በጉራ ፋርዳ ወረዳ በሪ በተባለ ቀበሌ አማራዎችን ብቻ ለይቶ በመሰብሰብ አንድ ግለሰብ ከክልል መጣሁ በማለት ከጠዋቱ አራት ሰዓት ገደማ ጀምሮ አማራዎችን ትጥቅ ማውረድ አለባችሁ የሚል ማስፈራሪያ አዘል መልዕክት ሲያስተላልፍ ነበር ብለዋል፡፡ እንደ አይን እማኖች ገለጻ ከክልል መጣሁ ካለው ግለሰብ ጋር የጉራ ፋርዳ ወረዳ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ የሆነች ግለሰብም አብራ በቦታው ስብሰባውን ስታስተባብር እንደነበር ገልጸው ግለሰቡ መኪናውን አስነስቶ ብቻውን እንደሄደ ታጣቂዎች ወደ እኛ በፍጥነት ሲመጡ በማየታችን በጫካ ውስጥ በመሮጥ ህይወታችንን ማትረፍ ችለናል ብለዋል፡፡ ምንጫችን ጨምረውም በዛሬው ዕለት በቀበሌው አምስት መቶ የሚደርሱ አማራዎች ሰብስበው እንደነበር ገልጸው የወረዳውና የዞኑ አመራሮች ለግድያው ተባባሪ በመሆናቸው አስፈላጊው እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮች ከጉራ ፋርዳ ምንጫችን ጋር ያደረግነው የስልክ ቃለ ምልልስ በዩቱዩብ ገጻችን ስለሚገኝ እንድትከታተሉት እንጋብዛለን፡፡ ዘጋቢ ፡-ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply