#አሁን የደረሰን መረጃ ወለጋ ኪራሞ .. በምስራቅ ወላጋ ከአማራ ክልል ሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኪራሞ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች በአማራ ዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተሰማ…

#አሁን የደረሰን መረጃ ወለጋ ኪራሞ .. በምስራቅ ወላጋ ከአማራ ክልል ሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኪራሞ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች በአማራ ዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተሰማ አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 28 /2013 ዓም ባህር ዳር … የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ እንደገለጹት በትናንትናው ዕለት ጥቅምት 27 /2013 ዓም ከአማራ ክልል ሰላሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የምስራቅ ወለጋ ክፍል ኪራሞ ወረዳ ላይ የኦነግ ታጣቂዎች በአማራ ማህበረሰብ አባላት ላይ ጥቃት በመክፈት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸዋቸውን የአይን እማኞች ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ እንደ ምንጫችን ገለጻ በዛሬው ዕለት የኦነግ ታጣቂዎች ከአካባቢው ወደ አማራ ክልል በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውመን ገልጸውልናል፡፡ በምስራቅ ወለጋ አብዛኞቹ አካባቢዎች በኦነግ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር እየዋለ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጫችን ከወዲሁ አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ ካልተቻለ በአካባቢው ከሚገኙ የአማራ ማህበረሰብ በተጨማሪ ከጎጃም ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ስጋት መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡ ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ተከታታዮቻችን ከምስራቅ ወለጋ ምንጫንን ከቦታው አናግረናል እንድትከታተሉት እንጋብዛለን፡፡ አሻራ ሚዲያ ከአካካባቢው ነዋሪዎች ጋር ያደረገውን ቆይታ ይዘን እንቀርባለን !! ዘጋቢ ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply