#አሁን የደረሰን ዜና ወለጋ ባቦ ወረዳ ሲርባ ቦኒ !!           አሻራ ሚዲ    ታህሳስ 13/2013 ዓ•ም ባህርዳር በአሁኑ ሰዓት 9:20 ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ…

#አሁን የደረሰን ዜና ወለጋ ባቦ ወረዳ ሲርባ ቦኒ !! አሻራ ሚዲ ታህሳስ 13/2013 ዓ•ም ባህርዳር በአሁኑ ሰዓት 9:20 ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ…

#አሁን የደረሰን ዜና ወለጋ ባቦ ወረዳ ሲርባ ቦኒ !! አሻራ ሚዲ ታህሳስ 13/2013 ዓ•ም ባህርዳር በአሁኑ ሰዓት 9:20 ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ባቦ ወረዳ ሲርባ ቦኒ ቀበሌ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከበባ ውስጥ እንደገባ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገለፁ። የኦነግ ሸኔ አባላት በቀበሌው ዙሪያ ከበው እንደሚገኙ እና እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ የመንግስት ንብረት የሆነን አንድ አንቡላንስ ያቃጠሉ ሲሆን የአንቡላንሱ ሹፌር በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም ሲሉ አክለው ገልፀዋል። ነዋሪዎቹ ለአሻራ ሚዲያ እንደገለፁት ከሆነ በአካባቢው ያለው የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ በሚደርሰው ግድያ እና ማፈናቀል ምክንያት ነዋሪዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉም ተናግረዋል። የመንግስት ተሽከርካሪ የሆነውን አንቡላንስ ያቃጠለው የኦነግ ቡድን ምሽቱን ወረ መንደሩ ገብተው ህዝባችን ላይ ጥቃት ከማድረሳቸው በፊት መንግስት ሊደርስልን እና ህይወታችንን ሊታደግልን ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል

Source: Link to the Post

Leave a Reply