አሁን ያለው የእልህ እና የፎክክር ፖለቲካ ስርአታዊ አካሄድ መሆኑ ያሰጋኛል አለ እናት ፓርቲ

ሀገር በእልህ እና በፎክክር አትቁምም ያለው እናት ፓርቲ ሀገሪቱን የሚመሩ አካላት ከየትኛውም ፓርቲ ተወልደው ይምጡ ፤የትኛውንም ፓርቲ ይፍጠሩ ቅድሚያ ለህዝብ ክብር መሰጠት አለባቸው ብሏል፡፡

የህዝብ ድምጽ በአግባቡ እየተሰማ አይደለም ያሉት የእናት ፓርቲ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ዳዊት ብርሃኑ የመገናኛ ብዙሀን የህብረተሰቡን ጭሁት ፤ድምፅን እያሰሙ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ይህ የሚያመለክተው ስርዓተ መንግስቱ የህዝን ድምፅ ቸል በማለት የተቀመጠ መሆኑን ነው የሚሉት አቶ ዳዊት ይህንን ጉዳይ የህዝብ ድምፅ እንዲሆኑ የተቋቋሞት ተቋማት ከማጋለጥ ይልቅ በማቆለጳጰስ ላይ ናቸው ይላሉ፡፡

«ምንም የማይካደው አሁን ያለነው በከባድ የኑሮ ውድነት ፤ግልፅ በሆነ ጦርነት ውስጥ ነው በዚህ መሃል ስለፓለቲካው ምንም የማያውቁ የህረተሰብ ክፍሎች እያለቁ መሆኑ ሁሉንም ሊሳስበው ይገባል » ብለዋል ከኤትዩ ኤፍ ኤም በነበራው ቁይታ፡፡

«መንግስት በእልህ እና በፎክክር በራሱ ህዝብ ላይ የድሮን ጥቃት እየፈጸመ ነው » የሚሉት አቶ ዳዊት «በዚህስ የሚገነባ ሀገር አለ ወይ?» ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

ባለስጣናቱ የህሊና በራቸውን ከፍተው እውነታው እንዲመለከቱም ጠይቀዋል፡፡

ፓለቲካ ሀሳብ በመሸጥ መንግሰት የሚገነባበት መንገድ እና ፍኖት መሆኑን የሚገልጹ አቶ ዳዊት ይህ ከሆነ ለምንድነው በጠረጲዛ ዙሪያ በመቀመጥ ችግሮችን በድርድ እና በንግግር የማይፈቱት ፡፡ይህ እኛን እንደፓርቲ ያሳስበናል ያስጨንቀናል ብለዋል፡፡

እናት ፓርቲ በተደጋጋሚ ችግሮች ሁል ጊዜም በድርድር እና በንግግር እንደፈቱ ከፍተኛ ጥረትን ከሌሉች ፓርቲች ጋር ሳደርግ ነበር ብሉናል፡፡

ያይኔ አበባ ሻምበል
ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply