'አለህም እንዳንል እንዲህ ይደረጋል የለህም እንዳንል ይመሻል ይነጋል' … የመተከል ጉዳይ ዛሬም! ምንአልባት ይታየው… … አማራው/አገው/ ከገጠሩ 100% ተፈናቅሏል :: በከተማ ያለ…

‘አለህም እንዳንል እንዲህ ይደረጋል የለህም እንዳንል ይመሻል ይነጋል’ … የመተከል ጉዳይ ዛሬም! ምንአልባት ይታየው… … አማራው/አገው/ ከገጠሩ 100% ተፈናቅሏል :: በከተማ ያለውም ጥቂት ነው:: በጥሪቱ በቀን ይዘረፋል:: … ሲጨፈጭፍ የነበረው ሀይል ግልገል በለስ መምህራን ኮሌጁ የተሀድሶ ስልጠና እየወሰደ ነው:: ስምምነቱ ትጥቅ አውርዶ እንዲገባ ቢሆንም የገባው ከነ ትጥቁ ነው:: ይህን የማነሳው በኮማንድ ፖስቱ ስራ ተስፋ ስላልቆረጥኩ አይደለም:: አሳፋሪ ስራው ድጋሜ እንዲገለጥ ስለምፈልግ ነው:: የራሱ ችግር የነበረበት ቢሆንም ተፈናቃዮች ተመልምለው የሚልሻ ስልጠና መውሰዳቸው አይዘነጋም :: ስልጠናውን የወሰዱት ተፈናቃዮች ሲጨርሱ ከተፈናቃዮች ካምፕ እንዲገቡ ተደረገ:: ትጥቁ ይሰጣቸዋል ቢባልም እስከ ዛሬ ምንም ነገር የለም:: የሚገርመው አብረው ሰልጥነው የነበሩ የጉሙዝ ወጣቶች ታጥቀዋል::ተፈናቃዮች አሁን ያሉበት ሁኔታ ሞትን ያስንቃል :: … የአርዲ ወንዝ ሲሞላ ወደ ተፈናቃዮች መጠለያ ይገባል:: ጎርፍ ፍራሽና የእርዳታ ቁሳቁሶችን ይዞባቸው ይሄዳል:: ከርሀብ በተጨማሪ ህፃናትን ቢምቢና ብርዱ ለህመም ዳርጓቸዋል:: ኮማንድ ፖስቱ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ወደ ቀያቸው እመልሳለሁ ብሎ ቃለ በል ከሆነ ሶስት ወር አለፈው:: … በመተከል የሚንቀሳቀሱ አማፂ ቡድኖች አሁንም ስልጠናቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል:: ዱራ ወንዝን ተደግፈው በሳስ ጫካ ያለው ጦር የሚጠብቀው ከሞት የተረፈውን አማራ ለመግደል ነው:: … ይህ ቡድን ሬሽን ከ5-8 አመት የሚያቆይ ሰብስቧል:: ሬሽኑ የተፈናቃዮች ጥሪት ነው:: ይህ ቡድን ወገኖቻችንን ካፈናቀለና ከገደለ በኋላ ሀብት ንብረታቸውን ዘርፏል:: ፍየልና ከብቶቻቸውን ዘርፎ እያረደ እየበላ ነው:: ስልጠናው አሁንም እንደቀጠለ ነው:: … ከአሶሳ በመንጌ:በሸርቆሌ: በኩምሩክ ወደ ሱዳን እየሄዱ ተመልሰው በጉባ ባፕራሮ ላይ ስልጠና እየወሰዱ ነው:: ባፕራሮ ከጉባ በቅርብ ርቀት ያለ ቦታ መሆኑን ልብ ይሏል:: … ከዚህ ስልጠና የሚወጡ ወደ አባይ ግድብ ቁሳቁስ ጭነው የሚሄዱ ሾፌርና ንፁሀን ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ:: … ለምሳሌ ከህዳሴ ግድቡ በ10ኪ.ሜ በምትገኘው ማንጎ ሰፈር ላይ በዚህ ሳምንት ብቻ 3 ጊዜ ጥቃት ተፈፅሟባታል:: ከ17 በላይ ተገድለዋል :: ……………………………………………………………… የአስቸኳይ ምግብ ጉዳይ ! … የመተከል ህዝብ አርሶም ሆነ ነግዶ መኖር ካቆመ ሶስት አመት አለፈው:: ተንቀሳቅሶ ለመስራት ዋስትና በማጣቱ አማራጩ ስደትና ርሀብ ሆኗል:: … ወጣቶች በሱዳን በረሀ የእባብና የጊንጥ ሰለባ ሆነዋል:: እናቶችና አዛውንቶች ርሀብና ብርዱ እየገረፋቸው መሪና ወገን አልባ ሆነው በካምፕ ዛሬም በሰቆቃ እየኖሩ ነው:: … ተፈናቃዮች አሁን የሚያስፈልጋቸው:- 1. በሶ:- እየበጠበጡም ሆነ በሚፈልጉት መንገድ መጠቀም ስለሚችሉ:: 2. ልብስ:- ቢቻል ብርድ ልብስ ባይቻል ግን ለክረምት የሚሆኑ ሁለገብ ወፍራም ልብስ 3. ስኳር:- ስኳርን በውሀ ብቻ በጥብጦ መጠጣት አንዱ የነብስ አድን መንገድ ነው:: 4. ድንኳን:- አሁን ከተሰራው ተጨማሪ ድንኳን ያስፈልጋቸዋል:: ተፈናቃዮች አሁን ካሉበት ወደ ደረቃማ ቦታ ላይ ቢሆኑ የተሻለ ይሆን ነበር:: … እነዚህ ለአስቸኳይ ቢደርሱ በሚል እንጂ ከአሁን በፊት ሲቀርቡ የነበሩት የእርዳታ ቁሳቁሶች አያስፈልጉም ማለት አይደለም:: የትኛውም ጋዜጠኛ የተፈናቃዮችን ሁኔታ ለመጠየቅ አይፈቀድም:: በአዲስ የተዋቀረው ኮሚቴ የሚመጡ እርዳታዋችን በፍጥነት ለማከፋፈል እየሰራ ቢሆንም ከመንግሥት አካላት በሙሉ አቅም እየተደገፈ አይደለም:: ከሞት ያመለጡ ቁስለኞች የሚበሉትም የሚታከሙበት የላቸውም:: አማፂ ቡድኑ በድባጤ ወረዳ ሳስማንደን ቀበሌ በ07-09-2013ዓ.ም 12 ሰዋችን ገድሏል:: … ዛሬም የወገኖቻችንን ሰብል የሚበቃውን ያክል ከዘረፈ በኋላ ቀሪውን በምታዩት መልኩ በቡለን ወረዳ ዶቢ ቀበሌ ሲያቃጥል ውሏል::

Source: Link to the Post

Leave a Reply