አለማቀፍ ትብብር(ጎዓት)ከመተከል ለተፈናቀሉ አማራ /አገው እርዳታ አደረገ።        አሻራ ሚዲያ     ታህሳስ 11/2013ዓ•ም ባህርዳር በሃገረ አሜሪካ የተመሰረተው…

አለማቀፍ ትብብር(ጎዓት)ከመተከል ለተፈናቀሉ አማራ /አገው እርዳታ አደረገ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 11/2013ዓ•ም ባህርዳር በሃገረ አሜሪካ የተመሰረተው…

አለማቀፍ ትብብር(ጎዓት)ከመተከል ለተፈናቀሉ አማራ /አገው እርዳታ አደረገ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 11/2013ዓ•ም ባህርዳር በሃገረ አሜሪካ የተመሰረተው የጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብር (ጎዓት)(Gojjam Global Alliance) ማህበርና አባላት ከመተከል አውራጃ በግፍ ተፈናቅለውና ሃብት ንበረታቸውን በትነው ለረሃብና በሽታ ተጋላጭ በሆነ እጅግ አስከፊ ሁናቴ በቻግኒ ከተማ ለሰፈሩት የአገው/አማራ ተፈናቃዪች ለዕለት ደራሽ የሚሆን ጊዜያዊ እርዳታ ለግሷል:: ድርጅቱ እጅግ በርካታ በሆኑ እርዳታ እና እገዛ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ሁሉ እየተገኘ የበኩልን ሲያደርግ ቆይቷል ሲል የገለፀ ሲሆን አሁንም መቋጫ በሌለው የመተከል/አማራ ግዛት የንፁሀን ግድያ እና መፈናቀል ባሰከተለው ቀውስ በአዊ ዞን በቻግኒ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖቹ የዳቦ ዱቄት፣ ወተት፣ ሳሙና እና ሌሎች ግብአቶችን ገዝቶ ለተፈናቃዮች እንዲደርስ አድርጓል ። በመተከል የአማራ/አገው ዘር ማጽዳት ይቁም በሚል እርዳታ ያደረገው የጎጃም አለማቀፍ ትብብር በሃገር ቤት ውስጥ ሁነው ከ(ጎዓት) ጋር በመተባበር ይሄን የእርዳታ ስራ እንዲሳካ ያደረጉ ግልሰቦችን በቀፈናቃዮች ስም አመስግነዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply