አለማወቅ ድንቁርናን ይወልዳል ፊደል ቆጥረናል የሚሉ ነገር ግን ከጥናታዊ ማስረጃ ይልቅ በግምት እና በቡና ላይ ወሬ የተጠመዱ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሥራ ባሕል አስተምሮ ላይ በሚነዙት አሉባልታ ትዝብት ላይ ወድቀዋል። (ከጽሑፉ መጨረሻ ማስረጃ ቪድዮ ያገኛሉ)

=======ጉዳያችን =======አለማወቅ ኃጢአት አይደለም።አለማወቅ በማወቅ ስለሚስተካከል ችግር የለውም።ባለማወቅ ውስጥ ተጀቡኖ ወደ ድንቁርና መምዘግዘግ ነው ጥፋት የሚሆነው።የኢትዮጵያ የቀደመ ዘመን ስኬቷ የሚያውቋት ምሑራን (በየዘመኑ የነበሩት ጠቢቦቿ) ስለነበሯት ነው።ምሑር፣አዋቂ፣ጥበበኛ የሚሉት ቃላት ከሆነ የአውሮፓና የአሜሪካ ዩንቨርስቲ መመረቅ ብቻ ባልሆነበት ዘመን፣የኢትዮጵያ ነገስታቷ፣የእምነት መሪዎቿ እና ጸሓፊዎቿ ሁሉ ከልጅነታቸው ታሽተው፣ተሞርደው እና ስለው የሚወጡባቸው የዕውቀት ማዕድ የሚቋደሱባቸው ሁነኛ ማዕከላት ነበሯቸው። አውሮፓ እና አሜሪካ ደርሶ የጥናት ጹሑፍ አስረክቦ ከእዛ በኋላ አንድም መጽሓፍ ሳያነቡ

Source: Link to the Post

Leave a Reply