አለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የፊታችን ሰኞ እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ እንዳስታወቀው ÷ኮንፈረንሱ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን÷ ከጥቅምት 30 ቀን 2013 እስከ ህዳር 10 ቀን 2013 የሚካሄድ ይሆናል፡፡
በቪዲዮ በሚደረገው በዚሁ ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ መንግስትና በአለማቀፉ ቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት መካከል የዝግጅቱን አፈጻጸም የተመለከተ ስምምነት ይፈረማል ነው የተባለው፡፡
በኮንፈረንሱ የአለማቀፉ ቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ዓባል ሀገራት፣ የአፍሪካ የቴክኖሎጂና የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሮች፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ያሉ ልዩ ልዩ ተቋማት ተወካዮችና ወጣቶች ይገኛሉ ነው የተባለው፡፡

The post አለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply