አለም አቀፍ የኤድስ ቀን የማህበረሰብ መሪነት የላቀ የኤችአይቪ ኤድስ  መከላከል  በሚል መሪ ቃል ትናንት ተከብሯል።በአለም አቀፍ ደረጃ  ለ36 ለጊዜ እንዲሁም በሀገራችን  ለ35 ተኛ ጊዜ…

አለም አቀፍ የኤድስ ቀን የማህበረሰብ መሪነት የላቀ የኤችአይቪ ኤድስ  መከላከል  በሚል መሪ ቃል ትናንት ተከብሯል።

በአለም አቀፍ ደረጃ  ለ36 ለጊዜ እንዲሁም በሀገራችን  ለ35 ተኛ ጊዜ  የማህበረሰብ መሪነት የላቀ የኤችአይቪ መከላከል  በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡

የኤድስ  ቀን በየአመቱ ህዳር 21 ቀን  በተለያዩ መሪ ቃሎች የሚከበር ሲሆን የዘንድሮውም  በቀጣይ ማህበረሰቡ  የላቀ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ  ቁርተኝነቱን እንዲጨምር ያለመ መሆኑ በስካይ ላይት በነበረው መርሃ ግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጲያ በ1990 አም መጀመሪያዎች  የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት  በከፍተኛ ሁኔታ   ጨምሮ የነበር ቢሆንም መንግስታዊ እና ሀገር በቀል በሆኑ ተቋማት  እንዲሁም በማህበረሰቡ ጥረት የኤች አይቪ ስርጭት ምጣኔ 0.91 ሊደርስ መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

በ2030 የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭት የማህበረሰብ ስጋ እንዳይሆን የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱ የተገለጸ ሲሆን ይበለጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ህፍሎች ላይ ትኩረት ተሰቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

Source: Link to the Post

Leave a Reply