“አለን!” በሚል መሪ ቃል በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል የዙም ቴሌቶን ተዘጋጀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ  ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ…

“አለን!” በሚል መሪ ቃል በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል የዙም ቴሌቶን ተዘጋጀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ…

“አለን!” በሚል መሪ ቃል በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል የዙም ቴሌቶን ተዘጋጀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ዘርን መሰረት ያደረገ አሰቃቂ ጭፍጨፋ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ይገኛል። በዚህም መሰረት በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በመተከል እና በሌሎች ቦታዎች ላይ ጥቃት ለተፈፀመባቸው እና ተፈናቅለው በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን እርዳታ ለማሰባሰብ በ03/01/2021 በመካከለኛው አውሮፓ ሰዐት አቆጣጠር ምሽት 20:00PM እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ ሰዐት አቆጣጠር 2:00PM ላይ በዙም የእርዳታ ማሰባሰብ ቴሌቶን ተዘጋጅቷል። በዕለቱም ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ እንግዶች ተጋብዘዋል ለወገን ደራሽ ወገን ነው እና ዘርን መሰረት አድርጎ ጥቃት ለደረሰባቸው ወገኖች በቴሌቶኑ ላይ በመሳተፍ አጋርነታችንን እናሳይ። አዘጋጆች 1. የአማራ ማህበር በሆላንድ 2. የወልቃይት ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በአውሮፓ 3. አማራ ማህበራዊ መገናኛ መድረክ ዓለም አቀፍ 4. ሞገድ አማራ ማህበር አለም አቀፍ 5. አማራ ሚዲያ ማዕከል አለም አቀፍ 6. የአማራ ማህበር በሲውዘርላንድ 7. የኦስትሪያ አማራ ማህበር 8. የአማራ ወጣቶች ማህበር በኢትዮጵያ 9. የአርበኞች ግንባር ታጋዮች በጎ አድራጎት ማህበር 10. የሞረሽ ወገኔ የአማራ 11. የወልቃይት አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በአሜሪካ 12. የራያ-አማራ አፌር በሰሜን አሜሪካ 13. የፋኖ አማራ ድጋፍ ሰጭ ማህበር በእስራኤል 14. የአማራ ማህበር በጀርመን 15. የፋኖ አማራ ድጋፍ ሰጭ በካናዳ 16 . የአማራ ኮሚኒቲ በዩናይትድ ኪንግደም የዙም መግቢያ ኮድ በቀጣይ ቀናት የምናሳውቅ ሲሆን በተለያዩ ሚዲያዎች በተመሳሳይ ስዓት በቀጥታ ይተላለፋል። በግፍ ተፈናቅለው ለተደራቢ ችግር የተጋለጡ ንጹሀን ወገኖቻችንን እየደገፍን ማንነትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም እንታገላለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply