አለን አለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ስብስብ የአሸባሪውን እና የወራሪውን የትሕነግ ጦር በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፈው በጀግንነት ሲፋለሙ የተሰው የጎንደር አማራ ፋኖዎችን አስታወሰ፤ ለሰማዕታት…

አለን አለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ስብስብ የአሸባሪውን እና የወራሪውን የትሕነግ ጦር በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፈው በጀግንነት ሲፋለሙ የተሰው የጎንደር አማራ ፋኖዎችን አስታወሰ፤ ለሰማዕታት ቤተሰቦችም ድጋፍ አድርጓል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ አለን አለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ስብስብ የአሸባሪውን እና የወራሪውን የትሕነግ ጦር በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፈው በጀግንነት ሲፋለሙ የተሰው የጎንደር አማራ ፋኖዎችን ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2014 አስታውሷል። ዝግጅቱም ለጀግኖች ሰማዕታት የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ተጀምሯል። በእለቱ ከሰኔ 25 ቀን 2013 መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ለቆ መውጣቱ በመንግስት ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ላይ ከፈጸመው ዳግማዊ ወረራ ወዲህ ነተደረገው ተጋድሎ ውድ ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ጀግኖች ተወስተዋል። አለን ለ12 የጀግና ቤተሰቦችም ለእያንዳንዳቸው የ10 ሽህ ብር በድምሩ የ120 ሽህ ብር ድጋፍ አድርጓል። ከዚህ በተጨማሪም በ200 ሽህ ብር የተገዙ 300 ጫማዎችን በሰሜን ጎንደር የተለያዩ ግንባሮች ተሰልፈው አሸባሪውንና ወራሪውን የትሕነግ ጦር እየተፋለሙ ከሚገኙት የጎንደር አማራ ፋኖዎች መካከል ተወካዮቻቸውን ጎንደር ላይ ላገኘቸው ድጋፉን አበርክቷል። በዚህ አቶ ተመስገን ሰጣርገው የተባሉ የጎንደር አማራ ባለሃብት በነጻ በፈቀዱት በጃንተከል ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው ዝግጅት ላይ በርካታ የክብር እንግዶች፣ የማራኪ ክ/ከተማ አመራሮች፣ የጎንደር አማራ ፋኖዎችና ተወካዮቻቸው፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሰማዕታት ቤተሰቦች መገኘታቸውን አሚማ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል። በመድረኩ የመናገር እድሉን ያገኙት አለን አለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ስብስብን አመስግነዋል፤ ድጋፉም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። አለን አቅሙ እየጠነከረ ሲሄድ ከአማራ ፋኖዎች በተጨማሪም ቀደም ሲል፣ በቅርቡና በቀጣይም ስለሀገርና ስለወገን ሲባል ዋጋ ከከፈሉም ሆነ ከሚከፍሉ የፋኖ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሾችንና ሌሎችም ጎን እንደሚሰለፍ ባለሙሉ ተስፋ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመድረኩ ከተገኙት መካከል ከአማራ ፋኖ_ሻለቃ ስጦታው ዳኘው(ባሻ)፣ ከሀገር ሽማግሌዎች ታጋይ ዘለቀ አሰማራው፣ ከአመራር የማራኪ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንተነህ ሲሳይ፣ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን መ/ር ደመወዝ ካሴ በአማራ ላይ ቁጭትና ተነሳሽነት የሚፈጥር ንግግር አድርገዋል። በተመሳሳይ ከጠገዴ አርማጭሆና አካባቢው በጎ አድራጎት ማህበር ሻምበል ገብሩ ልይህ፣ ከአማራ ወጣቶች ማህበር ተስፋ፣ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ ኪሩቤል፣እንዲሁም የአለንን የጫማ ድጋፍ ከተረከቡት የፋኖ አባላት መካከል ሙሴ ብርሃን፣ ስለሽ ግርማይ፣ እሱባለው ጸጋውም አስተያየት ሰጥተዋል። የሰማዕታት ቤተሰቦችም አለን ያደረገውን ድጋፍ በአድናቆት እንደሚመለከቱት ገልጸው፤ ያልታዩ እንዲታዩ፣ ረዳት የሌላቸው እንዲታገዙ፣ በሌሎችም ጭምር እንዲደገፉ ጥሪ አድርገዋል። አለንን በመወከል በጎንደር የተገኙት አቶ መታገስ ገ/ሚካኤልም መድረኩን በመምራት አለን አለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ህብረትን በተመለከተ እስከ መድረኩ ፍጻሜ ድረስ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሲሰጡ ተደምጠዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply