
አለን እና ወሎ ቤተ አምሐራ የበጎ አድራጎት ማህበራት ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በማንነታቸው ተፈናቅለው ራያ ቆቦ አቧሬ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች አማራ በመሆናቸው ብቻ የተፈናቀሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወገኖች በሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ አቧሬ ተጠልለው ይገኛሉ። ከሰሞኑ በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ፣ መቅደላና ኩታበር ለሚገኙ ተፈናቃይ አማራዎች።ድጋፍ ያደረጉት አለን እና ወሎ ቤተ አምሐራ ግንቦት 30 ቀን 2013 ምሽት ላይ 450 ለሚሆኑ ተፈናቃዮች 76.5 ኩንታል የምግብ ዱቄት፣ 450 ሊትር ፈሳሽ ዘይት እና 450 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና ለተፈናቃዮች እገዛ ተደርገዋል። ወሎቤተ አምሐራ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሆነው በገንዘብ፣ በጊዜ እና በጉልበት ለተባበሩ አመስግኗል።
Source: Link to the Post