አላማችን ዩክሬንን መጠቅለል ነው—ዲሚትሪ ሜድቬዴቭየሩሲያ ምክትል የደህንነት ኃላፊ ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ዩክሬንን እስከምንጠቀልላት ድረስ ጦርነቱ ይቀጥላል አሉ፡፡ሜድቬዴቭ ዩክሬን በታሪክ የሩ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/uG_Q8EhroQJHKspQLHynBPzElgxyn0-qTquPIMKk84QOq-gabjfWR93F0SHKXSNMkY4ATIqviOOQCQ6yWyMr_JDai5oWGPXu2UkWCtUqrMuZe0lDn3udpX07TZDjC3EDcbS0sWTND_OAMH3bWCpXSef8yrYvf6DMIkML95yZ4cn07YVGkyWlncSd974IxZOkKnq6vRnEWmv5NU-4vkFe6Vj7_y6WH6mJ5bg6LVsN3Yw_XiUhPu5Pm3r3KODcNIMjn8ekbpk1j8bOEKQL7UKC2aW1lMy3z3S8rwSmEHuwbIWU3vJmvcwUz4lsT0kuRlb-DSApq6FytWlBjv1GY4-VaA.jpg

አላማችን ዩክሬንን መጠቅለል ነው—ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ

የሩሲያ ምክትል የደህንነት ኃላፊ ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ዩክሬንን እስከምንጠቀልላት ድረስ ጦርነቱ ይቀጥላል አሉ፡፡

ሜድቬዴቭ ዩክሬን በታሪክ የሩሲያ አካል ነች ወደ ቤቷ እንመልሳታለን ነው ያሉት።

የሩሲያ አካል የነበረችውን ዩክሬንን እስከምናሸንፍ ድረስ ጦርነቱ ይቀጥላል ብለዋል።
የሩሲያ አላማ ጦርነቱን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የዩክሬን መሪዎችን ከስልጣን አባሮ ሀገሪቱን ወደ ቀድሞው ቦታዋ መመለስ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

እሳቸው ይህን ያሉት ከሰሞኑ አንድ የዩክሬን ባለስልጣን በታሪክ የሩሲያ አካል አልነበርንም ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው የወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ንግግር ያደረጉት ዲሚትሪ ሜድቬዲቭ ጦርነቱ ይቀጥላል ብለዋል።

ሜድሜዴቭ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ባልደረባ አባቱ መረቀ ጋር በነበራቸው ቆይታም ሃገራቸው የምዕራባዊያንን የተስፋፊነት አባዜ ለመግታት ቆርጣ መነሳቷን ገልጸው፤ከአፍሪካና ሌሎች ሃገራት ጋር ደግሞ አጋርነትን ለማጠናከር ከመቸውም በላይ እንደምትሰራ ተናግረዋል፡፡
ሜድሜዴቭ በቅርቡ ጦርነቱን እስከ ኬይቭ እንገፋለን ማለታቸው ይታወሳል።

በአባቱ መረቀ

የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply