አልቃይዳ የመን ውስጥ ታጣቂዎቹ መገደላቸውን ገለጸ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-ae42-08db1eaf847e_w800_h450.jpg

የአረቢያ ባህረ ገብ መሬት አልቃይዳ የተባለው የጽንፈኛ እስላማዊው ቡድን ቅርንጫፍ ማዕከላዊ የመን ውስጥ ሁለት መሪዎቹ በድሮን ጥቃት እንደገደሉበት ተናገረ።

ቡድኑ አዘውትሮ በሚጠቀምባቸው ድረ ገጾች ላይ ባለፈው ዕሁድ እንዳለው የሚዲያ ጉዳዮች ኃላፊው እና አንድ ሌላ አባሉ ከጥቂት ቀናት በፊት መኖሪያ ቤታቸው ላይ በደረሰ የዩናይትድ ስቴትስ የድሮን ጥቃት ተገድለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የማዕከላዊ ሥለላ ድርጅት ሲአይኤ ተፈጽሟል ስለተባለው ጥቃት አስተያየት አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

ባለፈው ጥር ወር ተፈጽሟል በተባለ ሌላ የዩናይትድ ስቴትስ የድሮን ጥቃት ሶስት የአልቃይዳ አባላት መገደላቸው ተዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply