አልጄሪያ የሩስያውን ስፑትኒክ ቪየተሰኘውን የኮቪድ 19 ክትባት ልታመርት ነው

አልጄሪያ የሩስያውን ስፑትኒክ ቪየተሰኘውን የኮቪድ 19 ክትባት ልታመርት ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጄሪያ ስፑትኒክ ቪ የተሰኘውን የኮቪድ 19 ክትባት ልታመርት መሆኑን አስታወቀች፡፡

አልጄሪያ ክትባቱን ከሞስኮ ጋር በመተባበር ነው በመጪው መስከረም ወር ለማምረት ያቀደችው፡፡

በተጨማሪም በህንድ ክትባት በማምረት ዕውቅና ያለው ድርጅትም እገዛ እንደሚያደርግ ነው የተሰማው፡፡

አልጄሪያ ክትባቱን በአፍሪካ ለማዳረስ ማለሟንም የመድሐኒት ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በየካቲት ወር 50 ሺህ መጠን ስፑትኒክ ቪ ክትባት ከሩስያ መቀበሏ ይታወሳል፡፡

በሩስያ በኩል የቴክኖሎጂ ሽግግሩን ለማመቻቸት ሦስት ኮሚቴዎች መቋቋማቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

The post አልጄሪያ የሩስያውን ስፑትኒክ ቪየተሰኘውን የኮቪድ 19 ክትባት ልታመርት ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply