አመራሩ የከተማዋን ነዋሪ ስነልቦናዊ ፍላጎት በአግባቡ ተገንዝቦ ወደ ስራ ሊገባ ይገባል- ወ/ሮ አዳነች

አመራሩ የከተማዋን ነዋሪ ስነልቦናዊ ፍላጎት በአግባቡ ተገንዝቦ ወደ ስራ ሊገባ ይገባል- ወ/ሮ አዳነች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በ2013 ዓ.ም እቅድ ዙሪያ ከከተማው አመራሮች ጋር በአዳማ እየመከረ ነው፡፡
 
በምክክር መድረኩ ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች በዚህ ወቅት ከአመራሩ የሚመራበትን አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ አውድ በተለይ የከተማዋን አጠቃላይ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ እና የነዋሪውን ስነልቦናዊ ፍላጎት በአግባቡ ተገንዝቦ ወደ ስራ እንዲገባ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።
 
በተያዘው በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ለማከናወን የታቀዱ ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም አመራር በባለቤትነት ስሜት ሀላፊነቱን ለመወጣት ቁርጠኛ ሊሆን ይገባ ብለዋል ፡፡
 
በተጨማሪም በተጠናቀቀው የመጀመሪያ ሩብ አመት የተመዘገቡ መልካም አፈጻጸም በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን በማረም ለቀሪ ወራት የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል ።
 
ውይይቱ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ስርነቀል ለውጥ እንዲመጣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ አመራሩ በእውነት ፣በተነሳሽነትና በቁርጠኝነት ሊሠራ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው በውይይቱ ወደ መዋቅሩ አዲስ የተቀላቀሉ ኃላፊዎች በየተመደቡበት ተቋም የከተማዋን አስተዳደራዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ ለመቀየር ስለሚወጡት ኃላፊነት ፣ በዋና ዋና ግቦችና የትግበራ ስልቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝና የአመለካከትና የተግባር አንድነትን ለመፍጠር የጎላ ፋይዳ እንዳለው መናራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
 
በጋራ ውይይቱ የቢሮ ኃላፊዎች ፣የክፍለ ከተማና የወረዳ በአጠቃላይ ከ1 ሺህ በላይ ኮር አመራሮች ተሳትፈዋል።

The post አመራሩ የከተማዋን ነዋሪ ስነልቦናዊ ፍላጎት በአግባቡ ተገንዝቦ ወደ ስራ ሊገባ ይገባል- ወ/ሮ አዳነች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply