አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶች መቀበል መጀመሩን የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል፡፡ታህሳስ 19 የሚከበረው አመታዊው የቅ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/ezvHkxLyEj7AIXAbjv5JfwydtgbT5BegiGVBtZDd-KQ1t24CwnW87A6dQvyNy0nefeBtf9TSHuWQR5O_YmPoYAlK2Y1xDKTZoMiGUmgtatU2Koy3GCS8h8EMKQ0uGOtvSvMhrBJxz9IJ-0ratPBgKXbSgNhD5qBcy01UgXM8P4HSeSX-eqr4JEH1QVAgohSqtS5PYI29DnLUpOlNcGSJeOFT9-jXpd4ZrCwyx7RkHH-FdyAATzyPv0BVKDO-YWtgc4Cd79JgcygvMPJTu8HmSfo0zKqxrUWM6cREu4ryqrpwimBEKPEEnJv7-wyUW6V69Hc6ds0dzyEkZOYSZNrJPA.jpg

አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶች መቀበል መጀመሩን የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል፡፡

ታህሳስ 19 የሚከበረው አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በጸጥታ መዋቅር ግብረሃይል የተለያዩ ዝግጅቶች በማከናወን እንግዶችን እየተቀበለ እንደሚገኝ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮሃላፊ አቶ ወሰንየለህ ስምኦን ተናግረዋል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶች ከመላው አለም አመታዊ የንግስ በዓሉን ለማክበር ወደ ሃዋሳ ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት ሃላፊው ከሆቴል ቁጥጥር ጀምሮ በንግዶች ላይ ተጨማሪ ዋጋ እንደይደረግ እንዲሁም በከተማዋ በካሜራ የታገዘ ክትትል ለማድረግ ዝግጅት መከናወኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የንግስ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የትራፊክ ፍሰቱን ምቹ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን፤ የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ከሚገኝበት ከፒያሳ እስከ ሃይቅ ድረስ ለተሸከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ዛሬ ማምሻውን በከተማ መስተዳደሩ በዓሉን ያለ ትራፊክ መጨናነቅ ለማበር ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ እንደሚደረጉም ገልጸዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

ፎቶ—-ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply