አመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓልን ለመታደም ወደ ሃዋሳ የሚመጡ ምእመናን ስጋት እንዳያድርባቸው እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓልን ለማክበር ወደ ሀዋሳ የሚያቀኑ ታዳሚዎች በቤተክርስቲያን አካባቢ ችግር ቢገጥማቸው ቀጥታ ውሳኔ የሚተላለፉባቸው ተዘዋዋሪ ችሎቶች በየአካባቢው መቋቋሙን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የ2013 ዓ.ም የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ካገኘ ወዲህ የሚከበር የመጀመሪያ ክብረ በዓል ነው፡፡በዚህም የተነሳ ወደ ሃዋሳ የሚያቀኑ ታዳሚዎች ስጋት እንዳይፈጥርባቸው የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ምክትል ኃላፊ ቅድስት ደሜ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በርካታ ቁጥር ያላቸው ታዳሚዎች ለአመታዊ ክብረ በዓሉ ወደ ሀዋሳ ስለሚጓዙ የትራንስፖርት፤ የአልጋና የምግብ እንዲሁም ሌሎች የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ የፀጥታ አካላት የስምሪት ትዕዛዝ ደርሷቸዋል ተብሏል፡፡በቤተክርስቲያን አቅራቢያ የሚፈጠሩ ወንጀሎች ቢኖሩ እንኳን በቀጥታ ውሳኔ የሚሰጡ ተዘዋዋሪ ችሎቶች መዘጋጀታቸውን ምክትል ሃላፊዋ ገልፀዋል፡፡

እንደ ምክትል ኃላፊው ገለፃ ከኃይማኖት አባቶች ከመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ከፀጥታ የስራ ሃላፊዎች የተውጣጣ ኮሚቴ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የፊታችን አርብ የመንገድ ማፅዳት እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሀ ግብር ያከናውናሉ፡፡

************************************************************************

ቀን 14/ 03/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply