አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ሥራ ማህበር አባላት 68.3 ሚሊዮን ወይንም…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/cU0HFdLL_GuD-5DIH3njq6F9MRJqFa0yU5SpzRkeSMWJ3wZr91WnFr6qw_IkIOmBJXchgsRfRGTExDKeQqY174GF-8qf22FOdAk8BRE7lHmRCD8UXau8B_EZIoOty3hW3y5pAFDbSIdfCkJE7Nk14gQ8zWztmJmCB63mhhBfSVR9_bmwDwvZa7ecWPKLxSaD6iCeAlS8p8KdKyN7603vtu4N0UCXsIh7Lqc-Nq2F18GlrJ5-x2jJn7vRQ1jneKvLs2i7OK07K2vRXcj3qwYAP-QVfyFBzwELDsuHe4V3bbbz_lOxbLgduzZvHstlVxZMNN_DduI4nch3JQ3D-1i3AA.jpg

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ሥራ ማህበር አባላት 68.3 ሚሊዮን ወይንም ከ51.84 በመቶ ትርፍ ማግኘታቸው ተነግሯል።

ተቋሙ 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በባለፈው በጀት አመት የስራውን አፈፃፀሙ የተሻለና 68.3 ሚሊዮን ብር ትርፍ የተመዘገበበት እንደሆነ በመድረኩ ተነስቷል።

አሚጎስ ካተረፈው ዓመታዊ ትርፍ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆነው ለህብረት ስራ ማህበሩ መጠባባቂያ ተቀማጭ እንደሚሆንም ተነግሯል።

በባለፈው ዓመት በመንፈቅ አመቱ አጠቃላይ የአባላቱን ቁጥር 5 ሺህ ማድረሱንና ለ8 መቶ 25 አባላቱ ከ 8 መቶ 86 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱንም ሰምተናል።

ተቋሙ 1 ቢሊዮን ብር ሃብት ማፍራቱንም በጠቅላላ ጉባኤው ላይ አስታውቋል ።

አሁን ላይ የአባላቱን ቁጥር ከ 7 ሺህ 5 መቶ በላይ ማድረሱንም ሰምተናል።

በአባቱ መረቀ

ግንቦት 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply