
አማራነታችን የመከራችን ምንጭ ሆኖ አይቀጥልም ‼️የአማራ ህዝባዊ ኮምቴ ነገ መጋቢት 24 ቀን ስለሚካሄደው ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ሰልፍ ያስተላለፈው መልዕክት መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ነገ እሁድ መጋቢት 24/2015 ዓ.ም በመላው አማራ ታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ ይደረጋል ።ባህር ዳር ከተማ እና ጀግና ህዝቦቿ በዕለቱ ለሚደረገው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አስፈላጊውን ዝግጅት ጨረሳለች ። ነገ መጋቢት 24 ይዞብን የመጣው ሁሉን አቀፍ ጥቃት ፣የዘር ማፅዳት ፣ጅምላ መፈናቀል እና መሳደድ ነው ።በወለጋ ፣በመተከል በማንነታችን ብቻ ፤አማራ ሆነን በመገኘታችን ብቻ እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ተጨፍጭፈናል ፣ተፈናቅለናል በአጠቃላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ተፈፅሞብናል ።በወለጋ የሆነብን እና የደረሰብን ሁሉ አንረሳም ። በላባችን የሰራነው ቤታችን በአማራነታችን ፈርሷል ።በላባችን አርሰን ያዘመርነው የእለት ጉርሳችን የቻሉትን ዘርፈዋል ፤መዝረፍ ያልቻሉትን የእሳት እራት አድርገውታል ። ምን ያልደረሰብን መከራና ስቃይ አለ? ይህ ሁሉ የሆነው መዋቅራዊ እና ስርዓታዊ በሆነ ሁኔታ ነው ።በመሆኑም ይህ መንግስታዊ ስርዓት አማራን በጠላትነት የፈረጀ ፣መዋቅራዊ በሆነ መልኩ የአማራን ህዝብ ሁሉን አቀፍ ጥቃት የሚያደርስ ስለሆነ መወገድ አለበት ። ስለሆነም በመጭው እሁድ በመላው አማራ ምድር ለሚደረገው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ሁላችን በምንገኝበት የከተሞች አደባባይ በመውጣት ይህንን አስከፊ ስርዓት እንቃወም ዘንድ የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ የከበረ ጥሪውን ያቀርባል ። ህልውናችን በክንዳችን‼️ የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post