አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የመጣውን ሃይል ጊዜ ሳንሰጠው ለመደምሰስ ወደ ግንባር እንዘምታለን ሲሉ የፎገራ ወረዳ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅም…

አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የመጣውን ሃይል ጊዜ ሳንሰጠው ለመደምሰስ ወደ ግንባር እንዘምታለን ሲሉ የፎገራ ወረዳ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን ባለው መሰረት በንፁሃን ዜጎች ላይ የግፍ ግፍ እየፈፀመ አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት እየሰራ ያለና ለክልላችንና ለወረዳችን የህልውና አደጋ ሁኗል ብለዋል። ያሉት የመንግስት ሰራተኞች በህዝባዊ ማዕበል የመጡትን የሽብርተኛ ቡድን እኛም ፆታ ሃይማኖት የትምህርት ደረጃ ሳይገድበን በህዝባዊ እንቅስቃሴ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ወደ ግንባር እንዘምታለን። ከመቸውም በበለጠ አካባቢያችን ከሰርጎ ገብና ከባንዳዎች መጠበቅ አለብን ፤ የዘማች ቤተሰቦች ድጋፍና እንክብካቤ ከዚህ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት በማለት አስተያየት ሰጥተዋል። የፎገራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቀ በሬ እንደገለጹት አሸባሪው የትህነግ ቡድን መደበኛና መደበኛ ያልሆነ ሃይል በማሰለፍ ከሞራልና ከሰብዓዊነት በታች ድርጊቶችን እየፈጸመ የሚገኝ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል እያደረሰብን ይገኛል። ዛፉን ለማድረቅ ቅርንጫፉን ሳይሆን ስሩን መምታት እንደሚባለው ሰሞኑን በአየር ሀይላችን የሽብር ቡድኑ ወሳኝ ቦታዎች ከፍተኛ ድብደባ እየደረሰበት አቅማቸው እየመነመነ የመጣ ቢሆንም ንቀን ልንተዋቸው አይገባም። ጠላት የጎረሰው ብቻ ነው ያለው የጎረሰውን እስኪውጥ ድረስ ብዙ ጉዳት ያደርሳል። ስለዚህ ጠላትን እንደጎረሰ በዚያው መቅበር አለብን ያሉት ምክልትል አስተዳዳሪው ሁላችንም በተደራጀ መንገድ አካባቢያችን ከሰርጎ ገቦችና ከባንዳዎች ከመጠበቅ ባሻገር በሚፈለገው ልክ የሎጅስቲክ ስራ መስራት፤ ግንባር ድረስ መዝመት ያለበት በመዝመት ጠላትን እስከ ወዲያኛው መቅበር አለብን በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ያለው የፎገራ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply