አማራዊ ማንነታቸው ተጠቅሶ ለዘመናት ህጋዊ ሆነው ግብር ሲከፍሉበት የነበረው የእርሻ መሬታቸው እንደተወሰደባቸው፣ በተጨማሪም ብሶታቸውን ለሚዲያ በመናገራቸው በደል እየደረሰባቸው መሆኑን በምዕራ…

አማራዊ ማንነታቸው ተጠቅሶ ለዘመናት ህጋዊ ሆነው ግብር ሲከፍሉበት የነበረው የእርሻ መሬታቸው እንደተወሰደባቸው፣ በተጨማሪም ብሶታቸውን ለሚዲያ በመናገራቸው በደል እየደረሰባቸው መሆኑን በምዕራ…

አማራዊ ማንነታቸው ተጠቅሶ ለዘመናት ህጋዊ ሆነው ግብር ሲከፍሉበት የነበረው የእርሻ መሬታቸው እንደተወሰደባቸው፣ በተጨማሪም ብሶታቸውን ለሚዲያ በመናገራቸው በደል እየደረሰባቸው መሆኑን በምዕራብ ሸዋ ዞን የዳኖ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ቅሬታቸውን ለአሚማ ያቀረቡት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በዳኖ ወረዳ አይላዳሌ ቀበሌ ለበርካታ ዓመታት ነዋሪ ሲሆኑ ለመሬታቸውም ህጋዊ ሆነው ለመንግስት ግብር ሲከፍሉ እንደነበር ገልፀዋል። ይሁን እንጅ ከሚያዚያ እና ግንቦት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ማሳቸውን አለስልሰውና አፅድተው ወደ እርሻ እየገቡ ባሉበት ወሳኝ ጊዜ አማራነታቸው ተጠቅሶ፣ ህገ ወጥ ናችሁ ተብለው ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ሄ/ር መሬት ብቻ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። በአይላዳሌ ቀበሌ በዚህ መልኩ ለዓመታት ይዘው ሲያለሙበትና ግብር ሲከፍሉበት የነበረውን የእርሻ መሬት ነጥቀው ለወጣት በሚል እድሜያቸው ላልደረሱ ህጻናት ሸንሽነው ማከፋፈላቸው ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮባቸዋል። መሬታቸው የተወሰደባቸውም ከ400 በላይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ለአቤቱታ ከቀበሌ እስከ ክልልና ፌደራል ድረስ ቢያቀኑም ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸው መቸገራቸውን ተናግረዋል። መሬታቸው ከመወሰዱም በላይ በእርሻ ወቅት ከተሰጣችሁ ማሳ ውጭ ገፍታችኋል የሚልና መሰል ሰበብ በመፍጠር 1,200 ብር ያለ ምንም ህጋዊ ደረሰኝ በአይላዳሌ ቀበሌ አስተዳዳሪ በአቶ ተካ ቡርጃ በኩል እንድንከፍል እየተደረግን ነው ሲሉ አማረዋል። በተጨማሪም ለሚዲያዎች መረጃ ሰጥታችኋል በሚል 6 የምንሆን ቅሬታ ያቀረብን አርሶ አደሮች በብርቱ እየተፈለግን ነው ብለዋል። ከመካከላቸውም አቶ ተስፋ መኳንንት የተባሉ አርሶ አደር ታህሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአይላዳሌ ቀበሌ ለስብሰባ ተጠርተው ከሄዱበት የወረዳ አስተዳዳሪው አቶ ወንድአፍራሽ ሙሊሳ ባሉበት በፖሊሶች ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸው ተገልጧል። ኢሳት ላይ ሲናገሩ የተነሱትን ፎቶ በማሳየት፣ አንተን ብሎ ቅሬታ አቅራቢ፣ ምን ብለህ ነበር የተናገርከው በሚል ድብደባ የተፈፀመበት መሆኑን የገለፁት አርሶ አደር የእኛም እጣፈንታ እንደ እሱ ነው የሚሆነው በሚል ከአካባቢው ለመሸሽ ተገደናል ብለዋል። ስለጉዳዩ ያነጋገርናቸው በምዕራብ ሸዋ ዞን የጃኖ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወንድአፍራሽ ሙሌሳ መሬታቸውን ህጋዊ አደረግን እንጅ አልነጠቅናቸውም ሲሉ አስተባብለዋል። የተደበደበ ሰው ስለመኖሩም የማውቀው ነገር የለኝም ያሉት አቶ ወንድአፍራሽ ለጥያቄያችን በቂ ምላሽ ሳይሰጡ ስልካቸውን ጀሮአችን ላይ ዘግተዋል። የአይላዳሌ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ተካ ቡርጃ በበኩላቸው ለአማራ ብቻ ሳይሆን ከሀረር ለመጡ ኦሮሞዎችም ይዘውት ከነበረው መሬት ሁለት ሁለት ሄ/ር በመስጠት ህጋዊ አድርገናል ብለዋል። ያለደረሰኝ ቅጣት በሚል ከ30 በላይ አርሶ አደሮችን ማሳ ገፍታችኋል በሚል ለእያንዳንዳቸው 1,200 ብር ማስከፈላቸውን ያመኑት አቶ ተካ ይህ የሆነው በአካባቢው ማህበረሰብ ውሳኔ ነው ብለዋል። ስለተደበደበው አርሶ አደር ግን የማውቀው ነገር የለም ሲሉ ያስተባበሉት አቶ ተካ ጥያቄያችን ሳንጨርስ ስልካቸውን ዘግተዋል። ከቅሬታ አርሶ አደር፣ከዳኖ ወረዳ አስተዳዳሪ እነሰ ከአይላዳሌ ቀበሌ አስተዳዳሪ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply