አማራ ለሀገር ያበረከተው ውለታ እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮ በኢትዮጵያ ምድር በአራቱም ማዕዘን እየተሳደደ ይገኛል ሲሉ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ገለጹ፡፡…

አማራ ለሀገር ያበረከተው ውለታ እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮ በኢትዮጵያ ምድር በአራቱም ማዕዘን እየተሳደደ ይገኛል ሲሉ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ገለጹ፡፡…

አማራ ለሀገር ያበረከተው ውለታ እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮ በኢትዮጵያ ምድር በአራቱም ማዕዘን እየተሳደደ ይገኛል ሲሉ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ገለጹ፡፡ አሻራ ሚዲያ ጥር፡-09/05/13/ዓ.ም ባህር ዳር በአሁኑ አማራ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ ያበረከተው ውለታ እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በአራቱም ማዕዘን በማንነቱ ምክንያት እየተገደለ ይገኛል ብለዋል፡፡ አማራ በባዶ እግሩ እየሄደ ሀገር የጠበቀ ቁርበት ፍቆ ታሪክ የፃፈ ድንጋይ ጠርቦ ቤተ መንግስት የገነባ አለት ፈልፍሎ ቤተ መቅደስ የሰራ እየሞተ ሀገር ያቆየ እየተራበ ሌላውን የሚያጠግብ ተካፍሎ የሚበላ እንግዳ ተቀባይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አማራ ክርስቲያኑ ከሙስሊሙ ሙስሊሙ ከክርስቲያኑ ጋር ተዋዶና ተፋቅሮ የሚኖር ደግና ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያ ባለውለታ ህዝብ መሆኑንም አንሰተዋል፡፡ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ እንደገለጹት አማራ ለሀገር ያበረከተውና ውለታው እንዲሁም ድካሙ እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጥሮ በኢትዮጵያ ምድር በአራቱም ማዕዘን እየተሳደደ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡ የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት በማሽን የፈለፈላቸው የግብር ልጆቹ አባታቸው ቢሞትኳን የአባታቸውን እኩይ ተግባር ይዘው በአማራ ህዝብ ላይ ያረቀቀውን የጥላቻ ደብተርና ያወጀውን የሞት አዋጅ ተቀብለው በአማራ ላይ ጦርነት ከከፈቱ ቆይተዋል ሲሉ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋ፡፡ አማራ ዛሬም እንደ ትናንቱ የመከራውን ፅዋ እየተጎነጨ ይገኛል ሲሉም አክለዋል። አማራ ለአለፉት ሰላሳ አመታት በሄደበት መጣልህ እየተባለ እየተባረረ እየተገደለ ከመሬቱ ከርስቱ ተፈናቅሎ ሀገር አልባ ሆኖ መቆየቱንም አንስተው በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በቡኖ በደሌ በወለጋ በጉራ ፈርዳ በመተከል በሸዋ በራያ በወልቃይት በመላው ኢትዮጵያ ተጨፍጭፏል አሁንም እየታረደ ይገኛል ብለዋል። በተለይ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ የአማራ እልቂት በመንግስታዊ መዋቅር እየተደገፈ አማራዎችን ሀገር አልባ ማድረጉና እያረዱ በዶዘር አርሶ መቅበሩ መቀጠሉን ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ለአማራ የእርግማን ምድር ሁናበታለች ብለዋል። በተለይ በመተከል ያለውን መከራ ስመለከት ጠቅላይ ሚንስቴር የአባይን ውሃ ለሱዳንና ለግብፅ ለቀው አባይን በአማራው ደም ለመገደብ ፈልገው ነው እላለው ሲሉ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ ተናግረዋል፡፡ የመተከል ምድር በአማራዎች ጎርፍ ሲጥለቀለቅ እያዩ አበባ እሚተክሉት መናፈሻ የሚሰሩት በአማራው ሞት እየተዝናኑ ይመስለኛል ሲሉም አክለዋል። በአለፈው አመት ወሎ ወልድያ ዩንቨርስቲ አንድ ኦሮሞ ተማሪ ተገደለ ብለው ዩንቨርስቲው ሞቱን ሳይሰማ እሳቸውና ሽመልስ አብድሳ ነበሩ መግለጫ ያወጡ ያሉት ምንጫችን አማራ በመተከልና በወለጋ እንደ ፋሲካ በግ ሲታረድ ኢትዮጵያ የአማራዎች የቄራ ምድር ስትሆን ጠቅላይ ሚኒስተሩ የት ገቡ ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪም በዘረኝነትና በአማራ ደም የተገነባ አቢዮት ይበለፅጋል ብሎ ማሰብ ከትግራይ ነፃ አውጭ አለመማር ነው ብለዋል። አያይዘውም ፍትህ በለለበት ዓለም ላይ ብልፃግና የለም ሲሉ ተናግረዋል። በመጨረሻም ፍትህ በግፍ ለታረዱና እየታረዱ ላሉ ወገኖቻችን ሲሉ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ጠይቀዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply