አማራ ሜዲካል ሪሊፍ ኢኒሼቲቭ (AMRI) እና ደጀን ለኢትዮጵያ ዘመቻ ሕልውናን በተመለከተ የምክክር እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር አከናወኑ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 30 ቀን…

አማራ ሜዲካል ሪሊፍ ኢኒሼቲቭ (AMRI) እና ደጀን ለኢትዮጵያ ዘመቻ ሕልውናን በተመለከተ የምክክር እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር አከናወኑ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሜዲካል ሪሊፍ ኢኒሼቲቭ (AMRI) እና ደጀን ለኢትዮጵያ ዘመቻ ሕልውናን በተመለከተ በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው በአልማ ህንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር አከናውነዋል። ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2014 ከረፋድ ጀምሮ በተካሄደው ዘመቻ ሕልውናን በተመለከተው የምክክር እና የገቢ ማሰባሰብ መርኃ ግብር ላይ ከ115 የማያንሱ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። እንደ አማራ የገጠመን አሁናዊ ሁኔታን በተመለከተ በዶ/ር አብራራው፣ ስለአጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ በዶ/ር ወንዶሰን፣ ስለስነ ልቦናዊ ጥንካሬ በዶ/ር ስመኘው፣ የሀገር ፍቅርና የጤና ባለሙያዎችን ጉዳይ በተመለከተ በልብስ ወርቅ ጌጡ መቅረቡ ተገልጧል። ኑ ለወገናችን በጋራ እንምከር!” በሚል በተዘጋጀው የዛሬው መድረክ በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር እስከ 160 ሽህ ብር በእጅ የተከፈለ እና ቃል የተገባ መሆኑ ታውቋል። አዳዲስ የጤና ፓኬጆችን አቅዶ መስራት፣ በወራሪው ትሕነግ የወደሙ ተቋማትን መገንባት፣ ተጎጅዎች በርሃብ እንዳይጎዱ መርዳት፣ ሙያዊ ስልጠና መስጠት፣ ከወቅቱ ጋር በተያያዘም ገቢ በማሰባሰብ ለተጎጅዎች መደገፍ የማህበሩ አላማዎች ናቸው። አዋላጅ ነርስ፣ፋርማሲስቶች፣ የራዲዮሎጅ ባለሙያዎች፣ ሪሰርቸሮች፣ ጤና መኮንኖችና ሌሎችንም በጤናው ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች የተካተቱበት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply