You are currently viewing 'አማራ ሺህ ጊዜ ቢደራጅ፣ ሺህ ጊዜ ቢሰለጥን፣ ሺህ ጊዜ ቢታጠቅ ፣ ሺህ ጊዜ ትክክል ነው!' ©ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ከባሕር ዳር ሰቤታሚት ወህኒ ቤት #መግቢያ የመልዕክቴ ርዕስ ያደረግኩት…

'አማራ ሺህ ጊዜ ቢደራጅ፣ ሺህ ጊዜ ቢሰለጥን፣ ሺህ ጊዜ ቢታጠቅ ፣ ሺህ ጊዜ ትክክል ነው!' ©ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ከባሕር ዳር ሰቤታሚት ወህኒ ቤት #መግቢያ የመልዕክቴ ርዕስ ያደረግኩት…

‘አማራ ሺህ ጊዜ ቢደራጅ፣ ሺህ ጊዜ ቢሰለጥን፣ ሺህ ጊዜ ቢታጠቅ ፣ ሺህ ጊዜ ትክክል ነው!’ ©ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ከባሕር ዳር ሰቤታሚት ወህኒ ቤት #መግቢያ የመልዕክቴ ርዕስ ያደረግኩት ጀግናው አርበኛ ዘመነ ካሤ በአንድ ወቅት የተናገረውን ነው። አባባሉ እውነት ሺህ ገዳይ ያለው ሕዝብ ለምን ሺህ ጊዜ አይታጠቅ። ከዚህ ቀጥሎ ያሰፈርኳቸው ሃሳቦች በጠቅላላው የእኔ የግል አስተያየቶች ናቸው። የመላው ፋኖ፣ እኔ የምሳተፍባቸው ተቋማት ወይም የግለሰቦችና የፋኖ መሪዎች አይደለም። #መንገዳችን አማራውም ይሁን ኢትዮጵያ የሚሄዱት በእነ ዘመነ ካሴ መንገድ ነው። ይህ መንገድ “ሺህ ጊዜ ሰልጥኖ፤ ሺህ ጊዜ የመታጠቅ መንገድ ነው። አማራ መንታ መንገድ ላይ ቆሟል፡፡ ከሁለቱ አንዱን መርጦ መቀጠል ግን ለነገ የማለው ምርጫ ነው፡፡ አንደኛው ጎዳና የአባቶቹ ነው፡፡ የተረጨበትን የአምሳ አመታት የውሸት ትርክት ጥላሸቱን አራግፎ መነሳት ነው። እንደንስር የርጅና ላባውን ነቃቅሎ ጥሎ በአዲስ ክንፍ ከወጀብ በላይ በኩራት መንሳፈፍ ይገባዋል። ክብር፣ ነጻት እና ማንነቱን ሌላ አካል ታግሎ እንዲሰጠው አሊያም እዲያስጠብቅለት መናወዝ የለበትም። ‘ስንሞት እንበዛን’ የሚል አስተሳሰብ በምድራዊ ጅምላ ጭፍጨፋ ብዙ ገፅ መያዝ የለበትም። የዚህ መንገድ መነሻው የሀቀኛ አማሮች ሀቀኛ ታሪክ ነው፡፡ ድል፣ ዙፋን፣ ክብር፣ ነጻት፣ ሀገር እና ትውወልድ የሚሻገር ታሪክ ነው፡፡ሁለተኛው መንገድ በአለፉት ስልሳ አመታት የተጓዝንበት አባቶቻችን ያልሄዱበት የማናቀው የውርደት ጎዳና ነው፡፡ መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መገደል፣ መራብ እና በማንነት ማፈር አማራው እንደህዝብ በምጣኔ ሀብት እና በማህበራዊ ሕይወቱ ውድቀት፣ የፖለቲካ ውክልናም ይሁን ተወካይ ድርቀት፣ የታሪክ፣ የባህል እና የእምነት ንቅዘት፣ የማንነት፣ የቋንቋ፣ የእሴት፣ ትውፊት እና ቅርሶች ውድቀት ፣ የምርምር፣ የፍልስፍና፣ የኪነ-ጥበብ፣ የቅኔ ውድቀትና እና የባለቅኔ ጠኔ መንሰራፋት ነው። አድር ባይነት እና ቅጥፈት ባህል የሆነባ፤ በአቋራጭ አጭበርብሮ፣ ዘርፎ፣ አስመስሎና ቀምቶ ስጋዊና ቁሳዊ ሰቀቀንን ማርካት፤ በእምነትና በመንፈስ መጠውለግ፣ መቀጨጭና መክሰም፤ ሰፊ ሀገር ቀርቶ እንደ እንስሳት በታጠረ በረት እያናወዙ ከጋጥ በጠበበ ‘ክልላዊ’ ማንነት እና እሳቤ ሰብአዊ ክብርን መርሳት ነው። እንደ ሀገር ቀልጠናል። ከዚህ ከፍ ሲል ዛሬ የታላቁ አማራ እና በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ነገዶች ህልውና አዳጋ ላይ ወድቋል፡፡ የ16ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የወረራ አደጋ በጋሀድ የመንግሥት ካባ አጥልቆ መጥቷል፡፡ አማራው በደምና አጥንቱ በቆረቆረው ከተማ የመግቢያ ቪዛ እየጠየቀ ነው፡፡መጥሪያዉ፣ መታወቂያው እና ምልክቱ የሆነችው ኢትዮጵያን እያጣ ነው፡፡ በመጣበት የውርደት ጎዳና ቀጥሎ እየተኮረኮመ መኖር አልያም የአባቶችን መንገድ መምረጥ ከፊቱ የተደቀኑ አማራጮች ናቸው። የአባቶቹን የአርበኝነት ታሪክ ተቀብሎ ራሱን በፋኖነት ማሰለፍ ደግሞ የመዳኛ መንገዱ ነው። #ፋኖነት እምነት፣ ቆራጥነት እና በአላማ መጽናት የፋኖነት አልፋና ኦሜጋ ነው፡፡ ፋኖነት ጦርነት አልያም ወረራ ሲነሳ ብቻ መሳሪያውን ወልውሎ ወደ ግንባር መትመም ማለት አይደለም፡፡ ፋኖነት አማራነት ነው። አማራ የሚያከናውናቸው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ክንዉኖች የፋኖነት አንድ አካል ነው ናቸው፡፡ ይቀድሳል፣ ቁርአን ይቀራል፣ ያርሳል፣ አገር ይጠብቃል። እንዲሁም አገር የስተዳድራል ወይም ይመራል። ቀዳሽነትን፣ አራሽነትን እና ተኳሽነትን (አገር ጠባቂነት) ለፋኖ ሰጥተን ሀገር ገዝነትን ለማን ልንሰጠው ነው? ዛሬ ላይ ያረጠው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አማሳዮች እና አሳላፊዎቻቸው “ፋኖ ፖለቲካ ውስጥ መግባት የለበትም፤ ፋኖነት እና ፖለቲካ ለየቅል ነው ነው” ሲሉ ደጋግመው ይደመጣሉ። የዚህ እሳቤ መነሻው የኢትዮጵያ አንድነት ጥላቻ ነው። ፋኖነት አማራነት ነው፤ አማራነት ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ አንድነት ነው። አብሮነት ነው። መገነጣጠል አልያም “እኔ ብቻ” የሚል እሳቤ አይደለም። የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ገዥወች ግን ከዚህ እሴቤ ፍፁም ተቃርኖ ላይ የቆሙ ናቸው፡፡ “ታላቋ ኦሮሚ” አልያም “ታላቋ ትግራይ” የሚሉ ናቸው። <<እኔ>> እንጂ <<እኛ>> የሚል ምልክት የላቻውም፡፡ ስለሆነም የእኛነት ባለቤቱ ፋኖ ፖለቲካውን በጥልቀት ተረድቶ የሀገር መሪነት ሚናውን ቢረከብ፤ እኛነት አልያም በሌላው ደምና አጥንት ላይ ሊገነቡ የታቀዱት ትናንሽ ግዛቶች ፍጻሜ ሆነ ማለት ነው፡፡ ፖለቲካውን በልኩ መረዳት፣ ማወቅ፣ መተንትን ተገቢው የአማራነትን መድረሻ አይቶ መታገል ተገቢ ነው፡፡ “ፋኖ ፖለቲካ ማወቅ የለበትም፤ ፖለቲካ ውስጥም መግባት የለበትም” የሚለውን የዘመኑ ተረኛ ገዥዎች ንግግር የአማራ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና እራሳቸው አንዳንድ ፋኖወችን ጨምሮ ሲያስተጋቡት ይደመጣል፡፡ ይህ የተሳሳተ ምልከታ ብየ አስባለሁ። የዚህ ሀሳብ በለ መብቶች የአማራነትን ይሁን የፋኖነትን መነሻ እና መዳረሻ በውል አጥርተው ያልለዩ የዘመኑ የሚዲያ ፕሮኮጋንዳ እንግርግቦቹ ናቸው፡፡ ፋኖነት ጥይት መተኮስ ለሚችል አማራ የተሰጠ ጸጋ ብቻ አይደለም፡፡ አማራ ለሆነ ሀኪም፣ መምህር፣ ነጋዴ፣ አርሶ አደር፣ መካኒክ፣ ሹፍር፣ አናጺ ወዘተ በተፈጥሮ አማራ በመሆኑ ብቻ አብሮነት ያለ ነው። ስለሆነም አንድ ፋኖ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብታዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቆቅልሽ ከሰፊው ማህበረሰብ በተለየ ሊረዳ ይገባል፡፡ ግዴታውም ነው። ለዚህ በቂ ማሳያ ማንሳት ግድ ይላል፡፡ በኢትዮጵያ የመሪነትም ይሁን የገዥነት ታሪክ በጉልህ ተስተዉሏ፡፡ በኢትዮጵያ የነበረው የመሳፍንት ዘመን አክትሞ ዘመናዊነት እንዲገነባ ብዙ ዋጋ የከፈለው አጼ ቴዎድረስ ቁጥር 1 ፋኖ ነበር። በወቅቱ ለነበረው የመሳፍንት እሳቤ “እምቢ” ብሎ በመፈነን ለዘመናዊት ኢትዮጵያ መሰረት አበጅቶ አልፏል፡፡ ንጉሥ ሀገር ጥለው ወደ እንግሊዝ በተሰደዱበት ወቅት ኢትዮጵያን ጠብቀው እየመሩ ያቆዩት እነአርበኛ ፋኖ በላይ ዘለቀ ናቸው፡፡ በዘመነ ኢሕአዴግ የአማራ ትግል እና ፋኖነት ዳግም እንዲጎለብት ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት ፋኖዎች በርካታ ናቸው። አሁንም እንደ ህዝብ መሰልጠን፣ ደራጀት፣ መታጠቅ አለብን። የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ እምዬ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ነው እየተጠነሰሱ ያሉት። ሁሉም ፋኖ አማራ ነው፡፡ ሁሉም አማራ ፋኖ ነው፡፡ ፋኖ መነሻ ያለው፤ መድረሻውንም አውቆ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ ፋኖ እያንዳንዷ የሚተኩሳትኀ ጥይት የፖለቲካ ምንዛሬ ውጤት መሆኗን ማወቅ አለበት፡፡ የአማራ ህዝብ ጠላት ትህነግ እና ኦነግ ብቻ ሳይሆኑ ዋነው ጠላትም የ4 ኪሎው ተረኛው ስርዓት መሆኑንም መረዳት አለብን፡፡ ፋኖነት ኩሩነት፣ በእምነት እና አላማ መጽናት እራሱን ሰውቶ ሌሎችን ማዳን ማለት ነው። ፋኖነት እንቢ ማለት ነው። “ሚስቴ ልጀ፣ እናቴ፣ አባቴ እና ራሴ” ከሚል ግለኝነት ወጥቶ “ሀገሬ፣ ህዝቤ ፣ስንደቄ፣ ባህሌ፣ ታሪኬና ማንነቴ” የሚል የጀግንነትን መንፈስ መውረስ ነው፡፡ ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 02/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply