አማራ በአንድነት መቆም ግድ የሚልበት ወቅት ቢኖር ዛሬ ነዉ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 03/2014/ አሻራ ሚዲያ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሚመራው ኦ…

አማራ በአንድነት መቆም ግድ የሚልበት ወቅት ቢኖር ዛሬ ነዉ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 03/2014/ አሻራ ሚዲያ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የሚመራው ኦፌኮ አማራ በኦሮሚያ ላይ ወረራ ፈፅሟል አለ። ወረራው የተፈፀመው በሸዋ እና በወለጋ አካባቢዎች ነው ብሏል። በምንጃር ሸንኮራ በኩል 280 ኪሎሜትር የኦሮሚያ ክልል ቦታ ወደ አማራ ክልል ገብቷልም ብሏል። በአማራ እና በኦሮሚያ በታሪክ ያለው ቁርሾ ተዳምሮ ዛሬ ጦርነት ከተቀሰቀሰ አይደለም ኢትዮጵያ ምስራቅ አፍሪካም ትረበሻለች ብሏል _ኦፌኮ። በሌላ በኩል መንግስት ከሸኔ ጋር የገባበትን ጦርነት በሰላም እንዲፈታ ያሳሰበው የኦፌኮ መግለጫ የኑሮ ውድነቱ መንስኤም የሰላም እጦት ነው ብሎታል። ችግሮች በሙሉ ፖለቲካዊ በመሆናቸው ፖለቲካዊ መፍትሄ ይፈልጋሉ ብሏል _ኦፌኮ። ኦፌኮ እና ኦህዴዳዊዉ ብልፅግና በአማራ ጉዳይ ያወጡት መግለጫ ተቀራራቢ ሲሆን፣ ብአዴናዊዉ ብልፅግና በጉዳዮ ሁሉ ዝምታን መርጧል። በሌላ በኩል አሁን ላለው ችግር ሁሉ መሰረቱ የአራት ኪሎው መንግስት በመሆኑ ትግሉ የሚያስፈልገው ወደ አራት ኪሎ ነው ብለዋል _አቶ ክርስቲያን ታደለ። የኑሮ ውድነቱም ሆነ የፀጥታ ችግሩ የሚፈታው አራት ኪሎ ባለው መንግስታዊ አስተዳድር በመሆኑ ትግሉ ወደ አራት ኪሎ ነው ብለዋል። አቶ ክርስቲያን ይሄን ይበሉ እንጂ አንዳንዶች የምን ትግል ነው በሚል በአቶ ክርስቲያን ላይ ተቆጥተዋል። እንደ አቶ ክርስቲያን፣ ዮሃንስ ቧያሌው፣ ፀጋ አራጌ አይነት ሰዎች ሲናገሩ እየተከተሉ የሚሳደቡ ተከፋዮች እንዳሉ ባለፈው አቶ ፀጋ አራጌ ተናግረው ነበር። ከብልፅግና በላይ ብልፅግና ሆነው ቁመው የአማራን ችግር የሚያራዝሙ ቅጥረኞች ጥቂት አይደሉም። ለአሻራ አስተያየቱን የሰጠ አንድ የፖለቲካ ልሂቅ እንዳለው በአማራ ላይ ጠላቶቹ ሁሉ ተስማምተውበታል። አማራ ግን በራሱ ጉዳይ መስማማት አቅቶት እርስ በእርሱ ይናከሳል። በዚህ ከቀጠለ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ እንዳሉት አማራ ከ500 ዓመት በፊት የገጠመው ውድመት ይደርስበታል። እውነት የሚናገሩትን እና የሚታገሉትን በመደገፍ፣ ሀሰተኞችን በማረም በአንድነት መቆም ግድ የሚልበት ወቅት ቢኖር ዛሬ ነው። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply