#አማራ ባንክበቀጣዩ አመት በርካታ ቅርንጫፎችን በመላው ሀገሪቱ እንደሚከፍት አማራ ባንክ አስታወቀበሀገሪቱ የባንክ ኢንደስትሪ ታሪክ በባለአክሲዮኖች ብዛት እና በከፍተኛ የተከፈለ ካፒታል ዘርፉ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/RHbNNpLdVLKN2y2_2hCLFekUXm1ga62stk6IdFpICw2Ss86a7Mojcu8zA0RJxjJA2jxFjf75-srX4fEjRyO6n4Y2QdUNxO1y5dKYX1GazXViMdE99Z_-G7BoxxkvQKjK-gzDZIxwGqURuoHciLAQtOK0LOOpdoTAFrQUte-OXeqJ8ujvGzIcBKIe2QofzY5pLaYrCl4lNZ33fVU074RMBhbvJ4ItFfOL0RJ9QU3IDNJdd7ISKoQkPNWmyaSL9rYCEP0mqCmabs08qDWrlhwbuQ8ujJtB4N8yd05gRBrtqvRiY6RfDdgMvvhJ5mySQWC58CDGzNbmGlssB6AclUdhcg.jpg

#አማራ ባንክ

በቀጣዩ አመት በርካታ ቅርንጫፎችን በመላው ሀገሪቱ እንደሚከፍት አማራ ባንክ አስታወቀ

በሀገሪቱ የባንክ ኢንደስትሪ ታሪክ በባለአክሲዮኖች ብዛት እና በከፍተኛ የተከፈለ ካፒታል ዘርፉን የተቀላቀለው አማራ ባንክ እስከ ሰኔ 30 2014ዓ.ም ቅርንጫፎቹን ወደ 100 እንደሚያሳድግ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ባንኩ ሰኔ 11 2014ዓ.ም ተመርቆ ስራ ሲጀምር በ72 ቅርንጫፎች አገልግሎት በመስጠት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ባንኩ ከባንክ ባሻገር የሚለውን ተቋማዊ ቃሉን መሰረት በማድረግ ሀሳብን በፋይናንስ በመደገፍ ብዙዎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀ የስራ ክፍል ማቋቋሙን የአማራ ባንክ የማርኬቲንግ እና ብራንዲንግ ዳይሬክተር አቶ አስቻለው ታምሩ ለኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ ተናግረዋል፡፡

ባንኩ በቀጣዩ አመት 2015ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ቅርንጫፎችን የመክፈት እቅድ እንዳለው አቶ አስቻለው ገልጸዋል፡፡

ከ6 ቢሊየን 516 ሚሊዮን ብር በላይ በተፈረመ የመነሻ ካፒታል እንዲሁም ከ4 ቢሊዮን 825 ሚሊዮን ብር በላይ በተከፈለ ካፒታል ባንኩ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል ።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply