አማራ ባንክ ከሕዳር 20 በኋላ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ አስታወቀ።የባንኩ የበላይ አመራሮች አቶ መላኩ ፋንታ እና የባንኩ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ በባንኩ ቀጣይ…

አማራ ባንክ ከሕዳር 20 በኋላ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

የባንኩ የበላይ አመራሮች አቶ መላኩ ፋንታ እና የባንኩ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ በባንኩ ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

አመራሮቹ በዚህ ጊዜ እንዳሉት የባንኩ አክስዮን መሸጫ ቀን ሕዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም ይዘጋል።

በመቀጠልም ከባንኩ አክስዮን ከገዙ 155 ሺህ ባለድርሻዎች ጋር የጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ወደ ስራ እንደሚገባ አመራሮቹ ተናግረዋል።

ባንኩ የአክሲዮን ሽያጭ ከጀመረበት ከነሀሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ያዝነው ጥቅምት ወር ድረስ ከ6 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ብር አክሲዮን መሸጡን አስታውቋል።

እንዲሁም ከተሸጠው አክስዮን ውስጥ ከ4 ነጥብ 8 ቢሊዮን በላይ ብር ደግሞ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለ ካፒታል አክሲዮን የሸጠ ሲሆን የመስራች ባለአክሲዮኑ ቁጥርም ከ155 ሺህ በላይ ደርሷል።

በጅብሪል ሙሃመድ
ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply