You are currently viewing አማራ ከሃዲዎችንና አድርባዮቹን በመለየት መታገል፤ ጀግኖቹን ደግሞ በትክክል ለይቶ ከጎናቸው በመሆን መከታነቱን በማሳየት ለሁለንተናዊ የለውጥ ትግል መነሳቱ ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ግ…

አማራ ከሃዲዎችንና አድርባዮቹን በመለየት መታገል፤ ጀግኖቹን ደግሞ በትክክል ለይቶ ከጎናቸው በመሆን መከታነቱን በማሳየት ለሁለንተናዊ የለውጥ ትግል መነሳቱ ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ግ…

አማራ ከሃዲዎችንና አድርባዮቹን በመለየት መታገል፤ ጀግኖቹን ደግሞ በትክክል ለይቶ ከጎናቸው በመሆን መከታነቱን በማሳየት ለሁለንተናዊ የለውጥ ትግል መነሳቱ ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ግዴታው ነው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ አብዝቶ ስለነገ እና ስለኢትዮጵያ በመጨነቅ ራሱን እና በርካታ ጀግኖቹን በየጊዜው አሳልፎ በመስጠት በበዛ ትዕግስት ውስጥ ነው ያለው! ትዕግስት በራሱ ክፉ አልነበረም! ግን ትዕግስትን እንደ ፍርሃት እና እንደሌላም የሚቆጥረው የተደራጀ እና የታጠቀ ፈርሃ እግዚአብሔር የሌለው፣ አውሬያዊ ባህርይው ያሸነፈው ፣ የንጹሃንን ደም በጅምላ በማፍሰስ መቼም የማይረካ ጸረ አማራ እና ጸረ ሀገር የሆነ ዘር አጥፊ እና አራጅ ቡድን እንደ በበዛበት ዘመን የበዛ ትዕግስቱ በእጅጉ ዋጋ እያከፈለው ነው! አማራ እጅግ የበዛ ትዕግስቱ ይህን በማይረዱትና ለመረዳትም በማይፈልጉት ስለነገ የማያስቡ፣ በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱ፣ የእሳቤ ድሃዎች፣ ዘረኞች፣ሴረኞች፣ የጥላቻ እና የሀሰት ትርክት ንጉሶችና ሰዋዊ አውሬዎች አማካኝነት በየጊዜው በሴራ በሚፈጸምበት የጭካኔ እልቂት የተነሳ አንድ ወይም ሁለት ጥቁር ቀን በሚል ብቻ ለመቆም የሚችል አልሆነም! ከጥቁር ቀን እና ከጥቁር የሀዘን ልብስ መልበስ በየጊዜው ከማዘንና ከመተከዝ፣ ጀግኖቹን ከመገበር ለመሻገር አልቻለም! ግን ይችላል! አማራ ከሃዲዎችንና አድርባዮቹን በመለየት መታገል፤ ጀግኖቹን ደግሞ በትክክል ለይቶ ከጎናቸው በመሆን መከታነቱን በማሳየት ለሁለንተናዊ የለውጥ ትግል መነሳቱ ተፈጥሮአዊ፣ ታሪካዊ እና ወቅታዊ ግዴታው ነው! “አማራ በሀሰት ትርክትና በጥላቻ ነሁልላችሁ ዘሬን አታጥፉ፣ በጅምላ አትገደሉኝ!” ብሎም መቆጣቱ ብሎም ወደ ትግል ማምራቱ ተፈጥሮአዊ ነው! እናም አንድ ሁለት ብለን ብለን ብንቆጥራቸው በየጊዜው በሴረኞች ምክንያት በተናጠልም ይሁን በጅምላ የሚያልቁ በየደረጃው ለወገናቸውን የድርሻቸውን ያበረከቱ የቁርጥ ቀን ልጆቹን ልብ በሚሰብር መልኩ ሲያጣ ነው የኖረው፤ በየጊዜው እያጣም ነው! ስንት ናቸው? ቤት ይቁጠራቸው! የአማራ ጥቁር ቀናት እጅግ ብዙ ናቸው! ራሱ ነው የሚያሳጥራቸው! ጠላት ብለው የፈረጁትማ ከምድረ ገጽ እስኪጠፋም ልጆቹን፣ ሚስቶቹን፣እናቶቹን፣ እህቶቹን፣ ወንድሞቹን፣ አባቶቹን፣ልጆቹን፣ወጣቶቹን፣ የትግል ፈርጦቹን በተናጠልም ሆነ በጅምላ ዘወትር መንጠቃቸው ከአፈጣጠራቸው ጎብጠው የተነሱበት እቅዳቸው፣ ትልቁ ስራቸው ነው! መወሰን መቻል ብሎም መሬት ላይ የሚታይ፣ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ እና ውጤት የሚያመጣ የነቃ፣ የተደራጀ እና የተናበበ ትግል በማካሄድ በድኩማኖች የተጫነበትን አሳዛኝ የመከራ ጊዜውን ማሳጠር ይችላል! እምቅ አቅሙም አለው! የሚቀረው ይህን እምቅ ከቀደምቶቹ የተቀዳ ታሪካዊ የጀግንነት መሰረቱን፣ የድል አድራጊነት፣ የአይበገሬነት፣ የፍትህ አዋቂነት፣ የአርበኝነት (የነፍጠኝነት)፣ ለሰንደቅ አላማ መስዋዕት ከፋይነት፣ የባንዳ ጠልነት፣ የሀገር ወዳድነት፣ አቃፊነት፣ የአርቆ አስተዋይነት፣ የጥበብ እና ህግ አዋቂነት፣ የለውጥ ፈላጊነት፣ የአብሮ የመኖር እና የተግባቦት እምቅ ችሎታውን በተደራጀ እና በተናበበ መልኩ በመስራት ራሱን ብሎም ሀገሩንና ወገኑን ለማዳን የሚያስችል ትግልን ማስቀጠሉ የጥቁር ቀን ጊዜውን ለመቀየር መሰረቱ ነው! አማራ በጣም ብዙ ጀግኖችን ያጣበት በሰኔ 15፣ በ17፣ በሰኔ 11 ወይም በሌሎች ጥቂት እርጉም ቀናት ብቻ የቆመ ጥቁር ቀን የለውም! በሽህዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን አማራዎች ማንነታቸው እንደ ወንጀል እየተቆጠረ በጅምላ ሲፈጁ ኖረዋል፤ አሁንም ቀጥሏል! ያ ሁሉ ለአማራ ጥቁር ቀኑ ነው! አማራ የሀዘን ጥቁር ካባውን በትግሉ መቀየር አለበት! ይችላልም! በማይካድራ፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ አውራጃ በጋዋ ቃንቃ መንደር፣ በሆሮ ጉድሩ ዞን ኪረሞ መርጋ ጅሬኛ፣ በመተከል ቡለን፣ በከማሼ፣ በአሶሳ፣ በአጣዬ፣ በሻሽመኔ፣ በቦቃ እንዲሁም በጭና፣ በቆቦ አጋምሳ በሌሎችም የተፈጸመው አውሬያዊ የዘር ፍጅት በምን ቃል ይገለጻል? ቃላት ምን አቅም አለው? በተናጠል በየቤቱ በመንግስታዊ ዘመቻ በግፍ እየተገደሉ፣ አስከሬናቸው በተሽከርካሪ እየተጎተቱ፣ የእምብኝ ባይነት፣ የህዝብ ተቆርቋሪነት፣ የትግል አዋቂነት፣ የእውነት ፈላጊነትና የአይበገሬነት እምቅ ታሪካቸው እንዳይነገርላቸው የተደረጉትን ትተን በየጊዜው ያለእረፍት በተለይም ላለፉት አራት ዓመታት ከሌሎች ሀገር ወዳድ ወገኖቹ ጋር በመሆን ደም እና አጥንቱን ገብሮ በሰራት ሀገሩ የተፈጸመት እና እየተፈጸመበት ያለው የጅምላ የዘር ፍጅት በእጅጉ አሳዛኝ ነው! ማንነቱንና አጽመ እርስቱን፣ ሀገሩንና ወገኑን በማለቱ፣ አብረን እንኑር በማለቱ የበዛ ትዕግስት በማሳየቱ ይሉንታ በማያውቁት ጸረ አማራዎች ጥምረት በእጅጉ ልብን የሚነካ የግፍ ግፍ ተፈጽሞበታል፤ እየተፈጸመበትም ነው! ይህን እጅግ የበዛ ግፍ፣ በደል እና ክህደት ለመግለጽ የሚያስችል ቃል የለም! ጥቁር ቀን በራሱ አይገልጸውም! ስለሁሉም ግን በየጊዜው በተናጠልም ሆነ በጅምላ እየተጨፈጨፉ ላሉ ወገኖቻችን ሁሉ ነፍስ ይማር በማለት ለዛሬውም ሆነ ለነገው ትውልድ በሚበጅ መልኩ ከበዛ አጉል ይሉንታ እና ትዕግስት በመውጣት ለአላማ እና ለውጤት መታገል የግድ ይላል! በህዝብ ልብ ውስጥ ተሻጋሪ ታሪክ ጥለው ያለፉ የጀግኖችን አደራ ለመወጣትና ለስር ነቀል ለውጥ ራስን ማዘጋጀትና ማብቃት፣ የለውጥ ብሎም የሀገር ባለቤት መሆንን ማረጋገጥ የመፈለግ እና ያለመፈለግ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የህልውና የመኖር እና ያለመኖር እንጅ! ይህ ሊሰመርበት ይገባል! የአማራው ፍትሃዊ ትግል ትናንትም አሸንፏል፤ ዛሬም ሆነ ነገ፣ ሁሌም በእርግጠኝነት ያሸንፋል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply