አማራ ክልል ጀውሃና ሰንበቴ ላይ ግጭት አለ

https://gdb.voanews.com/09320000-0a00-0242-3c08-08dafd8021af_tv_w800_h450.jpg

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ሰንበቴ ከተማና አካባቢው ዛሬ በመሣሪያ የታገዘ ግጭት እንደነበረ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አህመድ አሊ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ከትናንት በስትያም ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ጀውሃ ላይ ሌላ ግጭት እንደነበረ ተሰምቷል።

የሰንበቴው ግጭት የተቀሰቀሰው የጀውሃውን ሁኔታ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት መሆኑን ያመለከቱት አቶ አህመድ አሊ መንስኤውንና የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸው ሙሉነህ በጉዳዩ ላይ የክልሉ መንግሥት እየተነጋገረ መሆኑን አመልክተዋል።

ለዝርዝሩ ዘገባው የተያያዘውን ፋይል ይመልከቱ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply