አማራ ፋውንዴሽን ለፋኖ ድጋፍ አደረገ       አሸዳራ ሚዲያ    ጥር 14/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በቅርቡ የተቋቋመው የአማራ ፋውንዴሽን ለአማራ ፋኖ ማጠናከሪያ የ1.2 ሚ…

አማራ ፋውንዴሽን ለፋኖ ድጋፍ አደረገ አሸዳራ ሚዲያ ጥር 14/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በቅርቡ የተቋቋመው የአማራ ፋውንዴሽን ለአማራ ፋኖ ማጠናከሪያ የ1.2 ሚ…

አማራ ፋውንዴሽን ለፋኖ ድጋፍ አደረገ አሸዳራ ሚዲያ ጥር 14/2013 ዓ.ም ባህር ዳር በቅርቡ የተቋቋመው የአማራ ፋውንዴሽን ለአማራ ፋኖ ማጠናከሪያ የ1.2 ሚሊዮን ብር እርዳታ የለገሰ ሲሆን ለአማራ ልዩ ሀይል ደግሞ ከሰሞኑ ተመሳሳይ የ1.2 ሚሊዮን ብር እርዳታ እንደሚያበረክት ታውቋል፡፡ “አማራ ፋውንዴሽን ከተቋቋመ ቅርብ ጊዜው ቢሆንም በተቻለ አቅም ህዝባዊነታችንን ለማስመስከር በተግባር የተደገፈ ሚናችንን ለማበርከት ጥረናል ብሏል። ለአማራ ብሄረዊ ንቅናቄ (አብን) ገና በምስረታ ላይ እያለ 15 ሺህ ዶላር ሰብስበን አበርክተናል። ከዛም የራሳችንን ስራዎች ባቀድነው መሰረት እየሰራን ሲሆን በተጓዳኝ ደግሞ ወቅታዊ በሆኑና ትልቅ ዋጋ ባላቸው ህዝባዊ ጉዳዮች ላይም የበኩላችንን እያደረግን እንገኛለን ሲል ፋውንዴሽኑ አስታውቋል ። ከህዝብ የሰበሰብነውን ገንዘብ በመልክት ከማድረስና ሌላ ጭቅጭቅ ውስጥ ከመግባት እራሳችን ማድረስ አለብን በማለት የፋውንዴችናችን አመራሮች በአካል ተገኝተው ለፋኖ የተወሰነውን 1.2 ሚሊዮን ብር በአግባቡ ያስረከቡ ሲሆን ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ የተመደበውን 1. 2 ሚሊዮን ብር ደግሞ ሰሞኑን የርክክቡን ስነስርዓት የምትመለከቱት ይሆናል ሲል አጋርነቱን አሳይቷል። በተጨማሪም ይህ የአገር ቤቱ ፕሮግራማችን እንደተጠናቀቀ በትዕዛዝ በልዩ ጥራት ያስመረትናቸውን የፋውንዴሽናችን ሎጎ ያለባቸውን ምርጥ ምርጥ ምርቶችን ማለትም የፖሎ ኳሊቲ ቲሸርቶችን ( ለወንድና ለሴት ) ፣ የሚያማምሩ ኮፍያዎችን ( ለሴትና ለወንድ ) ፣ ቀበቶዎችን፣ ማስኮችን ፣ ማውዝ ፓዶችን ፣ ዣንጥላዎችን ….በብዛት በምርጥ ጥራትና ዲዛይን ቻይና አገር ድርጅት አወዳድረን አስመርተን የጨረስን ሲሆን በቅርቡም በእጃችን ይገባሉ ብሏል ፋውንዴሽኑ። እነዚህ ምርቶች በተጓዳኝ የምንሰራቸው የተጨማሪ ገቢ ማስገኛ መንገዶች ሲሆኑ ትላልቅ የቢዝነስ ተቋማትን አስጠንተን ስለጨረስን በቀጣይ በአሜሪካ አገር የእነዚህ ቢዝነስ ባለቤቶች በመሆን የማያቋርጥ የገቢ ምንጭ አማራጫችንን እጃችን እናስገባለን። አማራ ፋውንዴሽን ለአማራ ህዝብ በቁጭት የቆመ፣ በተግባር የሚገለፅ እውነተኛ የህዝብ አጋር እናደርገዋለን ሲል ፋውንዴሽኑ ለአማራ ህዝብ ያለውን አጋርነት አሳይቷል፡፡ ዘጋቢ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply