You are currently viewing “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ የካቲት ፩፬ ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ…

“አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ የካቲት ፩፬ ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ…

“አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ የካቲት ፩፬ ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጣችው የኒጀር ዜግነት ያላት የፊልም ባለሙያዋ ራህማቶ ኪታ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም በማድረግ አፍሪካዊያንም እንዲያውቁት ማድረግ ይገባል ብላለች። ባለሙያዋ የፍራንኮ አፍሪካን ፊልም አዋርድን አሸንፋለች። በሥራዎቿ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥታለች። የፊልም ጸሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ራህማቶ ኪታ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲኾን በአደባባይ ጥረት የጀመረችው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በማነጋገር መኾኑን አብራርታለች። በቅርቡም ይፋዊ ደብዳቤዋን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት መሥጠቷን አብራርታለች። በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የታየላት “የጋብቻ ቀለበቱ” የተሰኘው ፊልሟ በፊልሙ ዕይታ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳታፊዎችን ስም እና ምስጋናዋን በምትገልጽበት ቦታ፤ ጽሑፉን በአማርኛ ቋንቋ በማስፈር ቋንቋውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ጥረት አድርጋለች። በዓለማችን በርካታ ቋንቋዎች ያሉ ቢኾንም የራሳቸው የፊደል ገበታ ከታደሉ ጥቂት ቋንቋዎች መካከል አንዱ የኾነው አማርኛ ቋንቋ ፤ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ መኾን ይገባዋል፤ ይህንን ማድረግ ስንችል የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካውያንም ሐብት መኾን ይችላል ስትል ራህማቶ ኪታ አብራርታለች። የአማርኛ ቋንቋ 7ተኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እስኪኾን ጥረቴን አላቋርጥም ብላለች። አማርኛ ከምሥራቅ አፍሪካ ውጭ በእስራኤል፣በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች እና በደቡብ አፍሪካ በብዙዎች ዘንድ የሚነገር ውብ ቋንቋ ስለመኾኑ አብራርታለች። ዘገባው የአሚኮ ነው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply