አሜሪካም በአፍሪካ ጎዳና ( አሻራ ታህሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም) ምሽቱን የአሜሪካ ምክርቤት የጆን ባይደንን ፕሬዜዳትነት ለማፅደቅ ስብሰባ አድርጎ ነበር፡፡ በየፍርድቤቱ እና በየሚዲያው ምርጫው…

አሜሪካም በአፍሪካ ጎዳና ( አሻራ ታህሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም) ምሽቱን የአሜሪካ ምክርቤት የጆን ባይደንን ፕሬዜዳትነት ለማፅደቅ ስብሰባ አድርጎ ነበር፡፡ በየፍርድቤቱ እና በየሚዲያው ምርጫው…

አሜሪካም በአፍሪካ ጎዳና ( አሻራ ታህሳስ 29፣ 2013 ዓ.ም) ምሽቱን የአሜሪካ ምክርቤት የጆን ባይደንን ፕሬዜዳትነት ለማፅደቅ ስብሰባ አድርጎ ነበር፡፡ በየፍርድቤቱ እና በየሚዲያው ምርጫው ተጭበርብሯል ሲሉ የነበሩት ዶናልጅ ጆን ትራንፕ የውሸት ምርጫ ነው፣ አንቀበልም እያሉ በ11ኛው ሰዓት ለፈፉ፡፡… የትራንፕ ደጋፊዎችም የምክርቤቱን ዙሪያ በቁጥጥር ስር አውለው የምክርቤት አባላትን ተቆጣጠሩ፡፡ ወንበር እና መስኮት እየሰባበሩ አሸናፊው ትራንፕ ነው አሉ፡፡ አሜሪካ መር ማህበራዊ ሚዲያዎች ቲዊተር፣ ዮቲዮብ እና ፊስቡክ የትራንፕን ጦርነት ቀስቃሽ ልጥፎችን እየተከታተሉ አጠፉ፡፡፡ የአሜሪካ ልዮ ፖሊስም በትራንፕ ደጋፊዎች ላይ ተኩስ ከፈተ፡፡ አንዲት ሴትም ሞተች፡፡ ጆ ቫይደን ጉዳዮን ጋጠወጥነት የተቀላቀለበት አመፅ ሲሉት፣ ትራንፕ ደግሞ እውነት ፈላጊ አሜሪካዊያን ሲሉ ለአመፁ መሪዎች በዘወርዋራው ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ እንግሊዝ እና ካናዳ የአሜሪካ ዴሞክራሲ ውሃ እየበላው መሆኑን ተመልክተው አሜሪካዊያን ተረጋጉ እያሉ ነው፡፡ ትራንፕ ገና በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት አምገነንነትን ከዓለም አጠፋለሁ፡፡ መጀመሪያ ማስርም የዝንባብዌን መሪ ሙጋቬን ነው እያሉ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ በወቅቱ ሙጋቬ “አሜሪካ ያልተማረች እና አንድም የአዕምሮ ዶክተር እንደሌላት ያወቅሁት እብዱ ትራንፕ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሲሆን ነው” ሲሉ አሽሟጠዋቸው ነበር፡፡ በእርግጥም ፣ትራንፕ ወደ ቤተመንግስት እንደገቡ እብድ የሚያሰኛቸውን ንግግር እና ተግባርም ፈፅመው ነበር፡፡ በተለይ ስለ አፍሪካ የተናገሩት ንግግር የአፍሪካ ህብረት ሳይቀር አውግዞታል፡፡ ” አፍሪካዊያን ጥሩ የወሲብ አደራረግ እና ጭፈራ ከመቻል ውጭ በሌላ ነገራቸው በሙሉ ከሰው ያነሱ ሰነፎች ናቸው” የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፡፡ ነገር ግን ትራንፕ ይሄን ንግግር አላደረጉሁም ሲሉ ክደዋል፡፡ በሰሜን ኮርያ ጉዳይ ከወቅቱ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር “ሾዝ አቤ” ጋር ከተወያዮ በኃላ፣ አንድ የአሜሪካ ጋዜጠኛ ስለ ውይይቱ ይጠይቃቸዋል፡፡ እሳቸውም ” የአቤን የእንግሊዘኛ አስተርጓሜ ጡቷን እያየሁ፣ በውበቷ ተመስጨ ውይይቱን ብዙ አልተገነዘብኩትም” ነበር ብለውም መልሰዋል፡፡ የሜክሲኮ ደላላዎችን እና የእፅ ነጋዴዎችን ለማቆም ታላቅ አጥር ለማሳጠር ከመነሳታቸው በተጨማሪ፣ ሙስሊም ከሚበዛባቸው ሶማሌያን ጨምሮ ወደ አሜሪካ እንዳትገቡ ብለውም ከልክለው ነበር፡፡ ሙስሊም አሸባሪ ነው በሚለው ፈራጅ እና የጥላቻ ንግግራቸውም ዓለምአቀፍ ውግዘትን አስተናግደዋል፡፡ ትራንፕ የእስራኤልን ዋና ከተማ ከቴሌአቪቭ ወደ እየሩሳሌም ካመጡ በኃላ የፍልስጤም መሪዎች ትራንፕን ሲያወግዙ ” የደሃ ተቃውሞ በእርዳታ ይቆማል” የሚል ይዘት ያለው አሸማቃቂ ንግግር አድርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ ላይም አባይ ከተገደበ “ግብፅ ግድቡን ልታፈነዳው ትችላለች” ሲሉ ግጭት ቸርችረዋል፡፡ ስራ ከመስራት ይልቅ ተቀምጠው ቻይናን በመውቀስ የሚታወቁት ትራንፕ ኮሮናን ” ቻይና ቫይረስ” ብለው የሰየሙት ሲሆን፣ የዓለም የጤና ድርጅት ግን ዘረኝነት ያለበት ንግግር ነው ብሎ corona virus diesase 2019 – covid 19 ብሎ በአህፆረተ ቃል መጠሪያ እንዲሆን አድርጓል፡፡ ትራንፕ በመጀመሪያው አካባቢ ኮሮና የቻይና ተረት ነው እንጂ በሽታ አይደለም ያሉ ቢሆንም እሳቸውንም አሟቸው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ ወደ 300ሺ አሜሪካዊያንም በኮሮና ሙተዋል፡፡ ትራንፕ የአየር ንብረት ለውጥ የሚባል ነገር የለም፡፡ የቻይና ተረት ነው ብለው የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነትም ሽረዋል፡፡ ትራንፕ ተመድን፣የዓለም ጤና ድርጅትን፣ኔቶን የመሳሰሉ አለምአቀፍ ተቋማትን ሁሉ ለማውደም ሲዝቱ ነበር፡፡ ትራንፕ የሚጠሏት ቻይና ከስምንት ዓመት በኃላ የዓለም ልዕለ ሀያል ሀገር እንደምትሆን የአውሮፓ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ አሜሪካ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኃላ ከእንግሊዝ የበላይነቱን ነጥቃ ለ70 ዓመታት ያህል የዓለም ልዕለ ሀያል ሀገር ሆና ነበር፡፡ ይህ ግን እንደማይቀጥል ተረጋግጧል፡፡ የአሜሪካ ካፒታሊዝም በቻይና ኮሚኒዝም ተበልጦ በ2028 ቻይና የዓለም ልዕለ ሀያል ሆና አሜሪካን መምራት ትጀምራለች፡፡ አውሮፓውያን በአሜሪካ መንኮታኮት ብስጭት ውስጥም ገብተዋል፡፡ ከዓለም በኮሮና ተፅእኖ እንኳን ከፍተኛው ዕድገት የቻይና ሲሆን፣ ቻይና በኮሮና የያዘባት ህዝብ ቁጥር ከኢትዮጵያ በብዙ እጥፍ ያንሳል፡፡ ያውም የቻይና ህዝብ ከ1.3 ቢሊየን ወይም ከጠቅላላው የዓለም ህዝብ 23 ከመቶ ሆኖ እያለ በቻይና በኮሮና የታዙት በሺዎች የሚቆጠሩ ብቻ ናቸው ፡፡ አሜሪካዊያን ዛሬ እርስ በእርሳቸው ሲደባደቡ ” ቻይና እንዳታየን፣ ሩሲያ ሳቀችብን፣ ኢራን አላገጠችብን፣ ሰሜን ኮርያ አፌዘችብን” ሲሉ የልዕለ ሀይሏን አሜሪካ ክብር መውረድ በስጋት ገልፀዋል፡፡ የነጭ ፅንፈኛው ትራንፕ የአሜሪካ የቁልቁለት መንገድ መሪም ሆነዋል፡፡ ትራንፕን ብላዲሚር ፑቲን ናቸው ከከርሚሊን ቤተመንግስት ያስመረጧቸው እየተባለም በአሜሪካውያን ዘንድ ይጠረጠሩ ነበር፡፡ ፑቲን ግንበተደጋጋሚ እጀ የለበትም ብለዋል፡፡ ፑቲን በሳይቨር ጦርነት ወደር የለሽ መሪ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ በሰሞኑ ሁኔታዋ ፣ አሜሪካ ለ300 ዓመታት የተገነባ ህግ እና ተቋም ባይኖራት ኑሮ በዘር እና በአመለካከት ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ትገባ ነበር፡፡ ነገር ግን ገለልተኛ ተቋማት በመኖራቸው አሜሪካ ብትወዛወዝም ብዙ አትወድቅም፡፡ እንግዲህ ዛሬ አሜሪካ አፍሪካን ሆና አድራለች፡፡ አፍሪካስ መቼ ይሆን አሜሪካን የምትሆን?! አለመሆን የለም፡፡ ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያውያን መልካም የገና በዓል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply