“አሜሪካም ተጋላጭ ነች” – ፕ/ ጆ ባይደን

የራሳቸው ሃገር ለዴሞክራሲ አደጋ የተጋለጠች መሆኗን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ከትናንት ጀምሮ ለሁለት ቀናት የጠሩትን የዴሞክራሲ ጉባዔ እያስተናገዱ ናቸው።

ከመቶ በላይ ሃገሮች መሪዎችና የመንግሥታት ተጠሪዎች፣ የሲቪል ማኅበረሰቦችና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች የተገኙበት መድረክ አምባገነናዊነትን መጋፈጥ፣ ሙስናን መዋጋትና የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃን ማበረታታት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየመከረ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply